1
የዮሐንስ ወንጌል 19:30
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ “ተፈጸመ” አለ፤ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
Харьцуулах
የዮሐንስ ወንጌል 19:30 г судлах
2
የዮሐንስ ወንጌል 19:28
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከወዲሁ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉም ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተጠማሁ” አለ።
የዮሐንስ ወንጌል 19:28 г судлах
3
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
ኢየሱስም እናቱንና ይወደው የነበረውንም ደቀመዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን “አንቺ ሴት ሆይ! እነሆ ልጅሽ” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እናትህ እነኋት” አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27 г судлах
4
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ቀድሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤ ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ።
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34 г судлах
5
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
ይህ የሆነው “ከእርሱ አጥንት አይሰበርም” የሚለው የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም ሌላው የመጽሐፍ ክፍል “ያንን የወጉትን ያዩታል” ይላል።
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37 г судлах
6
የዮሐንስ ወንጌል 19:17
መስቀሉንም ተሸክሞ የራስ ቅል ወደሚሉት ስፍራ፥ በዕብራይስጥም ጎልጎታ ወደ ተባለው ቦታ ወጣ።
የዮሐንስ ወንጌል 19:17 г судлах
7
የዮሐንስ ወንጌል 19:2
ወታደሮቹም ከእሾህ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ አኖሩ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት፤
የዮሐንስ ወንጌል 19:2 г судлах
Нүүр хуудас
Библи
Тѳлѳвлѳгѳѳнүүд
Бичлэгүүд