1
የማቴዎስ ወንጌል 7:7
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤
Харьцуулах
የማቴዎስ ወንጌል 7:7 г судлах
2
የማቴዎስ ወንጌል 7:8
የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ በር ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።
የማቴዎስ ወንጌል 7:8 г судлах
3
የማቴዎስ ወንጌል 7:24
“ይህን ቃሌን ሰምቶ በሥራ ላይ የሚያውለው ሁሉ፥ ቤቱን በድንጋይ መሠረት ላይ የሠራ ብልኅ ሰውን ይመስላል።
የማቴዎስ ወንጌል 7:24 г судлах
4
የማቴዎስ ወንጌል 7:12
እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፥ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው።
የማቴዎስ ወንጌል 7:12 г судлах
5
የማቴዎስ ወንጌል 7:14
ወደ ሕይወት የሚያስገባው በር ግን ጠባብ ነው፤ መንገዱም አስቸጋሪ ነው፤ እርሱን የሚያገኙት ሰዎች ጥቂቶች ናቸው።
የማቴዎስ ወንጌል 7:14 г судлах
6
የማቴዎስ ወንጌል 7:13
“በጠባብዋ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚያስገባው በር ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነው። ወደዚያ የሚገቡትም ሰዎች ብዙዎች ናቸው።
የማቴዎስ ወንጌል 7:13 г судлах
7
የማቴዎስ ወንጌል 7:11
እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፥ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ፤ ታዲያ፥ በሰማይ ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን አይሰጣቸውም!
የማቴዎስ ወንጌል 7:11 г судлах
8
የማቴዎስ ወንጌል 7:1-2
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በእናንተ ላይ እንዳይፈረድባችሁ፥ በማንም ላይ አትፍረዱ፤ በሌሎች ላይ በምትፈርዱበት ፍርድ፥ በእናንተም ላይ ይፈረድባችኋል፤ እንዲሁም በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።
የማቴዎስ ወንጌል 7:1-2 г судлах
9
የማቴዎስ ወንጌል 7:26
ይህን ቃሌን ሰምቶ በሥራ ላይ የማያውለው ግን፥ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሞኝ ሰውን ይመስላል።
የማቴዎስ ወንጌል 7:26 г судлах
10
የማቴዎስ ወንጌል 7:3-4
በአንተ ዐይን ያለውን ግንድ ሳታይ፥ ስለምን በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጒድፍ ትመለከታለህ? ደግሞስ በአንተ ዐይን ግንድ እያለ፥ ወንድምህን ‘እስቲ በዐይንህ ያለውን ጒድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ?
የማቴዎስ ወንጌል 7:3-4 г судлах
11
የማቴዎስ ወንጌል 7:15-16
“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፥ በውስጣቸው ግን እንደ ነጣቂ ተኲላዎች ከሆኑት ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፤ እነርሱንም የምታውቁአቸው በሥራቸው ፍሬ ነው። ከእሾኽ ቊጥቋጦ የወይን ፍሬ፥ ከኮሸሽላስ የበለስ ፍሬ ይለቀማልን?
የማቴዎስ ወንጌል 7:15-16 г судлах
12
የማቴዎስ ወንጌል 7:17
እንዲሁም መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፤ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል።
የማቴዎስ ወንጌል 7:17 г судлах
13
የማቴዎስ ወንጌል 7:18
መልካም ዛፍ መጥፎ ፍሬ ማፍራት አይችልም፤ መጥፎ ዛፍም መልካም ፍሬ ማፍራት አይችልም።
የማቴዎስ ወንጌል 7:18 г судлах
14
የማቴዎስ ወንጌል 7:19
መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ፥ ተቈርጦ ወደ እሳት ይጣላል።
የማቴዎስ ወንጌል 7:19 г судлах
Нүүр хуудас
Библи
Тѳлѳвлѳгѳѳнүүд
Бичлэгүүд