1
የሉቃስ ወንጌል 6:38
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስጡ፤ ለእናንተም ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ እንዲሁ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም በጥሩ መስፈሪያ ታምቆና ተጠቅጥቆ እስኪትረፈረፍ ድረስ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል።”
Харьцуулах
የሉቃስ ወንጌል 6:38 г судлах
2
የሉቃስ ወንጌል 6:45
ስለዚህ ደግ ሰው ከመልካም ልቡ መልካምን ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከመጥፎ ልቡ ክፉውን ነገር ያወጣል። ሰው በአፉ የሚናገረው ከልቡ ሞልቶ የተረፈውን ነው።
የሉቃስ ወንጌል 6:45 г судлах
3
የሉቃስ ወንጌል 6:35
እናንተ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ! መልካም ነገርም አድርጉላቸው፤ ‘ብድራችን ይመለስልናል’ ብላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ይህን ብታደርጉ ዋጋችሁ ትልቅ ይሆናል፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጆችም ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለውለታ ቢሶችና ለክፉዎች እንኳ ሳይቀር ቸር ነው።
የሉቃስ ወንጌል 6:35 г судлах
4
የሉቃስ ወንጌል 6:36
የሰማይ አባታችሁ መሓሪ እንደ ሆነ እናንተም እንዲሁ መሓሪዎች ሁኑ።
የሉቃስ ወንጌል 6:36 г судлах
5
የሉቃስ ወንጌል 6:37
“በማንም ላይ አትፍረዱ፤ በእናንተም ላይ አይፈረድባችሁም፤ ሌሎችን አትንቀፉ፤ እናንተም አትነቀፉም፤ ይቅር በሉ፤ እናንተም ይቅርታ ታገኛላችሁ፤
የሉቃስ ወንጌል 6:37 г судлах
6
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28
“ለእናንተ ለምትሰሙኝ ግን እንዲህ እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም ነገር አድርጉ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚበድሉአችሁም ጸልዩላቸው፤
የሉቃስ ወንጌል 6:27-28 г судлах
7
የሉቃስ ወንጌል 6:31
ሰዎች ለእናንተ ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም እንዲሁ ለእነርሱ አድርጉላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 6:31 г судлах
8
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30
አንዱን ጒንጭህን በጥፊ ለሚመታህ፥ ሌላውንም ጒንጭህን እንዲመታ አዙርለት፤ ነጠላህን ለሚወስድብህ፥ እጀ ጠባብህንም ጨምረህ ስጠው፤ ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤ ንብረትህን የሚወስድብህን ሰው እንዲመልስ አትጠይቀው።
የሉቃስ ወንጌል 6:29-30 г судлах
9
የሉቃስ ወንጌል 6:43
“መልካም ዛፍ መጥፎ ፍሬ አያፈራም፤ እንዲሁም መጥፎ ዛፍ መልካም ፍሬ አያፈራም።
የሉቃስ ወንጌል 6:43 г судлах
10
የሉቃስ ወንጌል 6:44
ዛፍ ሁሉ በፍሬው ይታወቃል፤ ከእሾኽ የበለስ ፍሬ አይለቀምም፤ እንዲሁም ከእሾኻማ ቊጥቋጦ የወይን ፍሬ አይለቀምም።
የሉቃስ ወንጌል 6:44 г судлах
Нүүр хуудас
Библи
Тѳлѳвлѳгѳѳнүүд
Бичлэгүүд