1
የዮሐንስ ወንጌል 19:30
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ “ተፈጸመ” አለ፤ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
比較
የዮሐንስ ወንጌል 19:30で検索
2
የዮሐንስ ወንጌል 19:28
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከወዲሁ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉም ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተጠማሁ” አለ።
የዮሐንስ ወንጌል 19:28で検索
3
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
ኢየሱስም እናቱንና ይወደው የነበረውንም ደቀመዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን “አንቺ ሴት ሆይ! እነሆ ልጅሽ” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እናትህ እነኋት” አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27で検索
4
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ቀድሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤ ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ።
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34で検索
5
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
ይህ የሆነው “ከእርሱ አጥንት አይሰበርም” የሚለው የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም ሌላው የመጽሐፍ ክፍል “ያንን የወጉትን ያዩታል” ይላል።
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37で検索
6
የዮሐንስ ወንጌል 19:17
መስቀሉንም ተሸክሞ የራስ ቅል ወደሚሉት ስፍራ፥ በዕብራይስጥም ጎልጎታ ወደ ተባለው ቦታ ወጣ።
የዮሐንስ ወንጌል 19:17で検索
7
የዮሐንስ ወንጌል 19:2
ወታደሮቹም ከእሾህ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ አኖሩ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት፤
የዮሐንስ ወንጌል 19:2で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ