1
የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ኢየሱስም “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነና በእኔ የሚያምን ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽኝ?” አላት።
比較
የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26で検索
2
የዮሐንስ ወንጌል 11:40
ኢየሱስ “ካመንሽ የእግዚአብሔርን ክብር እንደምታዪ አልነገርሁሽምን?” አላት።
የዮሐንስ ወንጌል 11:40で検索
3
የዮሐንስ ወንጌል 11:35
ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።
የዮሐንስ ወንጌል 11:35で検索
4
የዮሐንስ ወንጌል 11:4
ኢየሱስም ሰምቶ “ይህ ሕመም ለሞት አይሰጥም፤ ይልቁንም ለእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ነው” አለ።
የዮሐንስ ወንጌል 11:4で検索
5
የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44
ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር ሆይ! ና፥ ወደ ውጭ ውጣ፤” ብሎ ጮኸ። ሞቶ የነበረውም ሰው እጆቹና እግሮቹ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ፤ ተዉት፤” አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44で検索
6
የዮሐንስ ወንጌል 11:38
ኢየሱስም በድጋሚ በጥልቅ ኀዘን ተውጦ ወደ መቃብሩ መጣ፤ መቃብሩም ዋሻ ነበረ፤ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር።
የዮሐንስ ወንጌል 11:38で検索
7
የዮሐንስ ወንጌል 11:11
ይህንንም ከተናገረ በኋላ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ፤” አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 11:11で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ