1
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:14
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ከማያምኑ ጋር አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋር ምን ድርሻ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
比較
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:14で検索
2
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:16
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:16で検索
3
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:17-18
ስለዚህም ጌታ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ፤ ርኩስንም አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ “ለእናንተም አባት እሆናለሁ፤ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ፤” ይላል ሁሉንም የሚገዛ ጌታ።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:17-18で検索
4
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:15
ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን ስምምነት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:15で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ