1
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል!
比較
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17で検索
2
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21
እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን ስለ እኛ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ኃጢአት አደረገው።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21で検索
3
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:7
የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:7で検索
4
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:18-19
ይህ ሁሉ የሆነው፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን፥ የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህ እግዚአብሔር የሰዎችን በደል ሳይቆጥርባቸው በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር አስታርቋል፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኑሯል።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:18-19で検索
5
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:20
ስለዚህ እግዚአብሔር ጥሪውን የሚያቀርበው በእኛ በኩል በመሆኑ፥ እኛ ለክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ስለ ክርስቶስ ሆነን “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:20で検索
6
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15-16
በሕይወትም ያሉት፥ ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ፥ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ። ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15-16で検索
7
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:14
አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች በመሆናችን፥ የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፤ ይህ በመሆኑም ሁሉ ሞተዋል።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:14で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ