1
ወደ ሮም ሰዎች 5:8
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ነገር ግን እኛ ኃጢአተኞች ሆነን ሳለ ክርስቶስ በእኛ ምትክ ሞቶአል፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ያስረዳል።
Összehasonlít
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 5:8
2
ወደ ሮም ሰዎች 5:5
በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ሞላ ተስፋው አያሳፍርም።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 5:5
3
ወደ ሮም ሰዎች 5:3-4
በዚህ ብቻ ሳይሆን መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝልን ስለምናውቅ በመከራችንም እንመካለን። ከትዕግሥትም በፈተና መጽናት፥ ከመጽናትም ተስፋ ይገኛል።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 5:3-4
4
ወደ ሮም ሰዎች 5:1-2
እንግዲህ እኛ ጽድቅን ያገኘነው በእምነት ስለ ሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን። ወደዚህ አሁን በእምነት ጸንተን ወደምንገኝበት ጸጋ የገባነው በእርሱ ስለ ሆነ በተስፋ የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች በመሆናችን እንመካለን።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 5:1-2
5
ወደ ሮም ሰዎች 5:6
ገና ደካሞች ሆነን ሳለ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች ሞተ።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 5:6
6
ወደ ሮም ሰዎች 5:9
እንግዲህ የጸደቅነው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሆነ ይበልጡንም ከእግዚአብሔር ቊጣ የምንድነው በእርሱ አማካይነት ነው።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 5:9
7
ወደ ሮም ሰዎች 5:19
በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ እንዲሁም በክርስቶስ መታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ይጸድቃሉ።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 5:19
8
ወደ ሮም ሰዎች 5:11
ይህም ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነትም በእግዚአብሔር እንመካለን።
Fedezd fel: ወደ ሮም ሰዎች 5:11
Kezdőoldal
Biblia
Olvasótervek
Videók