1
የሉቃስ ወንጌል 13:24
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“በጠባብዋ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ በዚህች በር መግባት የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን መግባት አይችሉም እላችኋለሁ።
Comparer
Explorer የሉቃስ ወንጌል 13:24
2
የሉቃስ ወንጌል 13:11-12
ከዚያም ከዐሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ርኩስ መንፈስ ጀርባዋን ያጐበጣት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋ ወገብዋ በመጒበጡ ቀና ለማለት በፍጹም አትችልም ነበር። ኢየሱስ ባያት ጊዜ ጠራትና “አንቺ ሴት ከበሽታሽ ተፈውሰሻል!” አላት።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 13:11-12
3
የሉቃስ ወንጌል 13:13
እጆቹን ጫነባት፤ ወዲያውም ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 13:13
4
የሉቃስ ወንጌል 13:30
ስለዚህ ኋለኞች ፊተኞች ይሆናሉ፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ።”
Explorer የሉቃስ ወንጌል 13:30
5
የሉቃስ ወንጌል 13:25
የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 13:25
6
የሉቃስ ወንጌል 13:5
አይደለም! ንስሓ ባትገቡ እናንተም እንደእነርሱ ትጠፋላችሁ እላችኋለሁ።”
Explorer የሉቃስ ወንጌል 13:5
7
የሉቃስ ወንጌል 13:27
እርሱም እንደገና ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም፤ እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ከእኔ ራቁ!’ ይላችኋል።
Explorer የሉቃስ ወንጌል 13:27
8
የሉቃስ ወንጌል 13:18-19
ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔር መንግሥት በምን ትመሰላለች? ወይስ ከምን ጋር አነጻጽራታለሁ? አንድ ሰው በአትክልቱ ውስጥ የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች፤ እርስዋ አድጋ ዛፍ ሆነች፤ ወፎችም በቅርንጫፎችዋ ላይ ጎጆአቸውን ሠሩ።”
Explorer የሉቃስ ወንጌል 13:18-19
Accueil
Bible
Plans
Vidéos