2 ቆሮንቶስ 6

6
1ከእግዚአብሔር ጋራ ዐብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን መጠን፣ የተቀበላችሁትን የእግዚአብሔርን ጸጋ ከንቱ እንዳታደርጉት ዐደራ እንላችኋለን። 2እርሱ፣
“በተወደደ ጊዜ ሰማሁህ፤
በድነት ቀን ረዳሁህ” ይላልና።
እነሆ፤ የተወደደው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው።
ጳውሎስ የተቀበለው መከራ
3አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ ለማንም ዕንቅፋት መሆን አንፈልግም። 4ይሁን እንጂ በምናደርገው ነገር ሁሉ ራሳችንን እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች እናቀርባለን፦ በብዙ ትዕግሥት፣ በመከራ፣ በችግር፣ በጭንቀት፣ 5በመገረፍ፣ በመታሰር፣ በሁከት፣ በሥራ ብዛት፣ እንቅልፍ በማጣት፣ በመራብ፣ 6በንጽሕና፣ በዕውቀት፣ በትዕግሥት፣ በቸርነት፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ በእውነተኛ ፍቅር፣ 7በእውነት ቃል፣ በእግዚአብሔር ኀይል፣ በቀኝና በግራ እጅ የጽድቅ የጦር ዕቃ በመያዝ፣ 8በክብርና በውርደት፣ በመመስገንና በመሰደብ ኖረናል፤ ደግሞም እውነተኞች ስንሆን ሐሰተኞች ተብለናል፤ 9የታወቅን ስንሆን እንዳልታወቅን ሆነናል፤ ሞተዋል ስንባል እነሆ በሕይወት አለን፤ ብንደበደብም አልተገደልንም፤ 10ሐዘንተኞች ስንሆን ሁልጊዜ ደስተኞች ነን፤ ድኾች ስንሆን ብዙዎችን ባለጠጎች እናደርጋለን፤ ምንም የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።
11የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፤ ሁሉን በግልጽ ነግረናችኋል፤ ልባችንንም ወለል አድርገን ከፍተንላችኋል። 12በእኛ አልተገደባችሁም፤ ነገር ግን በውስጣችሁ ተገድባችኋል። 13ልጆቼ እንደ መሆናችሁ መጠን ይህን አሳስባችኋለሁ፤ እናንተም በዚያው ልክ ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱልን።
ከማያምኑ ሰዎች ጋራ አለመተባበር
14ከማያምኑ ሰዎች ጋራ አግባብ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋራ ምን ግንኙነት አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋራ ምን ኅብረት አለው? 15ክርስቶስ ከቤልሆር#6፥15 በግሪኩ ቤልያር ጋራ ምን ስምምነት አለው? የሚያምን ከማያምን ጋራ ምን ኅብረት አለው? 16የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖታት ጋራ ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፤
“ከእነርሱ ጋራ እኖራለሁ፤
በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤
አምላካቸው እሆናለሁ፤
እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”#6፥16 ዘሌ 26፥12ኤር 32፥38ሕዝ 37፥27
17“ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡ፤
ተለዩም፤
ይላል ጌታ።
ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤
እኔም እቀበላችኋለሁ።”#6፥17 ኢሳ 52፥11ሕዝ 20፥34 እና 41
18“እኔ አባት እሆናችኋለሁ፤
እናንተም፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፤
ይላል ሁሉን የሚችል ጌታ።”#6፥18 2ሳሙ 7፥147፥8

S'ha seleccionat:

2 ቆሮንቶስ 6: NASV

Subratllat

Copia

Compara

Comparteix

None

Vols que els teus subratllats es desin a tots els teus dispositius? Registra't o inicia sessió