1
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:3-4
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ ላይ የምትፈርድ ያንንም የምታደርግ ሰው ሆይ! ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን? ወይስ የቸርነቱን፥ የቻይነቱን፥ የታጋሽነቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን? የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሓ ሊመራህ እንደሆነ አታውቅምን?
Сравни
Разгледайте ወደ ሮሜ ሰዎች 2:3-4
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:1
ስለዚህ አንተ የምትፈርድ ሰው ሆይ! የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ ፈራጅ የሆንከው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።
Разгледайте ወደ ሮሜ ሰዎች 2:1
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:11
በእግዚአብሔር ዘንድ ማዳላት የለምና።
Разгледайте ወደ ሮሜ ሰዎች 2:11
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:13
በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚፈፅሙት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙት አይጸድቁምና።
Разгледайте ወደ ሮሜ ሰዎች 2:13
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:6
እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል፤
Разгледайте ወደ ሮሜ ሰዎች 2:6
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:8
በራስ ወዳዶች፥ ለእውነት በማይታዘዙት ነገር ግን ለዐመፃ በሚታዘዙት ላይ ቁጣና መቅሠፍት ይመጣባቸዋል።
Разгледайте ወደ ሮሜ ሰዎች 2:8
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:5
ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሓ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን በራስህ ላይ ቁጣን ታከማቻለህ።
Разгледайте ወደ ሮሜ ሰዎች 2:5
Начало
Библия
Планове
Видеа