:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የጠራች ጠፈርን በህዋው ላይ አጸናት፤ የሰማይም መታየት በክብሩ ነው። ብርሃኑን ያሳይ ዘንድ ፀሐይን ያወጣል፤ የሰማይም ብርሃን ሥርዐቱ ድንቅ ነው ። በዋዕዩም ሀገሩን ያቃጥላል፤ ዋዕዩንስ ማን ይቋቋመዋል? ዋዕዩንም እሳት እንደሚነድድባት ምድጃ ያደርጋል፤ ፀሐይ ግን ከሦስት ጊዜ በላይ የበለጠ ተራሮችን ያቃጥላቸዋል። ከእርሱ የሚወጣው እሳታዊ ዋዕይ፥ የሚልከውም ብርሃን ዐይን ያጨልማል፤ የፈጠረው እግዚአብሔርም ታላቅ ነው፤ በቃሉም ፈጥኖ ይሄዳል።
ያጋሩ
ያንብቡ:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የተራሮች መኩሪያ፥ የጠራች የሰማይ ድባብ፥ የከዋክብት ውበት፥ ሞገስ ያላትም ትዕይንት ናት። ፀሐይ ብቅ ስትል፥ ጮራዋንም ስትፈነጥቅ፥ የልዑል እግዚአብሔር ሥራ ምንኛ ድንቅ ነው! በማለት ታበስራለች። ቀትር ላይ መሬትን ታደርቃለች፤ ሙቀቷንስ የሚቋቋም ማነው? ሙቀትንም ለማግኘት ወናፍን መንፋት አለብን፤ ፀሐይ ግን ተራሮቹን ሦስት እጥፍ ጊዜ ታነዳቸዋለች፤ እስትንፋሷ የእሳት ነበልባል፥ ጮራዋም አንጸባራቂና ዓይንን የሚያጥበረብር ነው። እርሷን የፈጠረ መንገዷንም በቃሉ የሚያፈጥን፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው።
ያጋሩ
ያንብቡ