መጽ​ሐፈ ሲራክ 43:1-5

መጽ​ሐፈ ሲራክ 43:1-5 አማ2000

የጠ​ራች ጠፈ​ርን በህ​ዋው ላይ አጸ​ናት፤ የሰ​ማ​ይም መታ​የት በክ​ብሩ ነው። ብር​ሃ​ኑን ያሳይ ዘንድ ፀሐ​ይን ያወ​ጣል፤ የሰ​ማ​ይም ብር​ሃን ሥር​ዐቱ ድንቅ ነው ። በዋ​ዕ​ዩም ሀገ​ሩን ያቃ​ጥ​ላል፤ ዋዕ​ዩ​ንስ ማን ይቋ​ቋ​መ​ዋል? ዋዕ​ዩ​ንም እሳት እን​ደ​ሚ​ነ​ድ​ድ​ባት ምድጃ ያደ​ር​ጋል፤ ፀሐይ ግን ከሦ​ስት ጊዜ በላይ የበ​ለጠ ተራ​ሮ​ችን ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል። ከእ​ርሱ የሚ​ወ​ጣው እሳ​ታዊ ዋዕይ፥ የሚ​ል​ከ​ውም ብር​ሃን ዐይን ያጨ​ል​ማል፤ የፈ​ጠ​ረው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላቅ ነው፤ በቃ​ሉም ፈጥኖ ይሄ​ዳል።