መዝሙር 108:2-5
መዝሙር 108:2-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የዐመፀኛ አፍና የኀጢአተኛ አፍ በላዬ ተላቅቀዋልና። በሽንገላ አንደበትም በላዬ ተናገሩ፤ በጥል ከበቡኝ፥ በከንቱም ተዋጉኝ። በወደድኋቸው ፋንታ አጣሉኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ። በመልካም ፋንታ ክፉን ከፈሉኝ። በወደድኋቸውም ፋንታ ጠሉኝ።
መዝሙር 108:2-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በገናና መሰንቆም ተነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ። ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ። ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና፤ ታማኝነትህም እስከ ሰማያት ትደርሳለች። አምላክ ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።