ሉቃስ 21:28-31
ሉቃስ 21:28-31 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ይህም ሁሉ በሆነ ጊዜ ወደ ላይ አቅንታችሁ ተመልከቱ፤ ራሳችሁንም አንሡ፤ የሚያድናችሁ መጥቶአልና።” ምሳሌም መስሎ እንዲህ አላቸው፥ “በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ። ለምልመውም ያያችኋቸው እንደ ሆነ መከር እንደ ደረሰ ታውቃላችሁ። እንዲሁ እናንተም ይህ እንደ ሆነ ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ደረሰች ዕወቁ።
ያጋሩ
ሉቃስ 21 ያንብቡሉቃስ 21:28-31 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እናንተም እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ተቃረበ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ፤ ራሳችሁንም ወደ ላይ ቀና አድርጉ።” ቀጥሎም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ “በለስንና ዛፎችን ሁሉ ተመልከቱ፤ ቅጠሎቻቸው አቈጥቍጠው ስታዩ፣ በዚያ ጊዜ በጋ መቃረቡን ራሳችሁ ታውቃላችሁ። እንዲሁ ደግሞ እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች ዕወቁ።
ያጋሩ
ሉቃስ 21 ያንብቡሉቃስ 21:28-31 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ። ምሳሌንም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ፤ ሲያቈጠቍጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች እወቁ።
ያጋሩ
ሉቃስ 21 ያንብቡ