የሉ​ቃስ ወን​ጌል 21:28-31

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 21:28-31 አማ2000

ይህም ሁሉ በሆነ ጊዜ ወደ ላይ አቅ​ን​ታ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አንሡ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ መጥ​ቶ​አ​ልና።” ምሳ​ሌም መስሎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በለ​ስ​ንና ዛፎ​ችን ሁሉ እዩ። ለም​ል​መ​ውም ያያ​ች​ኋ​ቸው እንደ ሆነ መከር እንደ ደረሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እን​ዲሁ እና​ን​ተም ይህ እንደ ሆነ ስታዩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እንደ ደረ​ሰች ዕወቁ።