የሉቃስ ወንጌል 21:28-31

የሉቃስ ወንጌል 21:28-31 መቅካእኤ

ይህም መሆን ሲጀምር መዳናችሁ ቀርቦአልና ቁሙ፤ ቀናም በሉ።” እንዲህ ሲልም ምሳሌ ነገራቸው “በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ፤ ሲያቈጠቁጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። እንዲሁ ደግሞ ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች እወቁ።