ኢያሱ 20:1-3
ኢያሱ 20:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በሙሴ ቃል የነገርኋችሁን የመማፀኛ ከተሞችን ስጡ። ባለማወቅ ሳይወድድ ሰውን የገደለ በዚያ ይማፀን ዘንድ፥ ለእናንተ የመማፀኛ ከተሞችን ሥሩ፤ ነፍስ የገደለ ሰውም በአደባባይ ለፍርድ እስኪቀርብ ድረስ በደም ተበቃዩ አይገደል።
ያጋሩ
ኢያሱ 20 ያንብቡኢያሱ 20:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “በሙሴ በኩል በነገርኋችሁ መሠረት የመማፀኛ ከተሞች እንዲለዩ ለእስራኤላውያን ንገራቸው፤ ሳያስበው ድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው ወደዚያ በመሸሽ ከደም ተበቃዩ እንዲያመልጥ ከተማዪቱ መጠለያ ትሁን።
ያጋሩ
ኢያሱ 20 ያንብቡኢያሱ 20:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ ሳይወድድ ሳያውቅም ሰውን የገደለ ገዳይ እንዲሸሽባቸው በሙሴ እጅ የነገርኋችሁን መማፀኛ ከተሞችን ለዩ፥ ከደም ተበቃዩ መማፀኛ ይሆኑላችኋል።
ያጋሩ
ኢያሱ 20 ያንብቡ