መጽሐፈ ኢያሱ 20:1-3

መጽሐፈ ኢያሱ 20:1-3 አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን፥ እንዲህ አለው፤ ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ “በሙሴ አማካይነት ባዘዝኳችሁ መሠረት የመማጠኛ ከተሞችን ለዩ፤ ማንም ሰው ሳያውቅ በድንገት ሰው ቢገድል፥ ወደዚያ በመሄድ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው ይድናል፤