ኢያሱ 14:6-9
ኢያሱ 14:6-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአምላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ቃል ታውቃለህ። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ፤ እኔም በልቡ የነበረውን ቃል መለስሁለት። ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞች ግን የሕዝቡን ልብ አስካዱ፤ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ እከተለው ዘንድ ተመለስሁ። ሙሴም በዚያ ቀን፦ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም በርግጥ ርስት ይሆናል’ ብሎ ማለ።
ኢያሱ 14:6-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የይሁዳም ሰዎች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ከዚያም የቄኔዛዊው የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ ስለ አንተና ስለ እኔ፣ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ የተናገረውን ታውቃለህ። የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ምድሪቱን እንድሰልል ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ፤ እኔም ትክክለኛውን ማስረጃ ይዤለት መጣሁ፤ ዐብረውኝ ወደዚያ የወጡት ወንድሞቼ ግን፣ የሕዝቡ ልብ በፍርሀት እንዲቀልጥ አደረጉ፤ ሆኖም እኔ አምላኬን እግዚአብሔርን በፍጹም ልቤ ተከተልሁት። ስለዚህም ሙሴ በዚያች ዕለት፣ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ተከትለኸዋልና እግርህ የረገጣት ምድር ለዘላለም የአንተና የዘርህ ርስት ትሆናለች’ ብሎ ማለልኝ።
ኢያሱ 14:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፥ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፦ ለአምላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ። የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ እኔም በልቤ የነበረውን ቃል መለስሁለት። ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ አቀለጡ፥ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ። ሙሴም በዚያ ቀን፦ አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም በእርግጥ ርስት ይሆናል ብሎ ማለ።
ኢያሱ 14:6-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አንድ ቀን ከይሁዳ ነገድ የሆኑ ሰዎች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ከእነርሱ አንዱ የቀኒዛዊው የይፉኔ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “በቃዴስ በርኔ በነበርንበት ጊዜ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ስለ አንተና ስለ እኔ የተናገረውን ታውቃለህ፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የዚህችን ምድር ሁኔታ ለማጥናት ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ የአርባ ዓመት ጐልማሳ ነበርኩ፤ ለእርሱም አስተማማኝ የሆነ ማስረጃ አቅርቤአለሁ፤ ከእኔ ጋር ሄደው የነበሩ ሰዎች ግን የሕዝቡ ልብ በፍርሃት እንዲቀልጥ አደረጉ፤ እኔ ግን ለአምላኬ ለእግዚአብሔር በታማኝነት ታዛዥ ሆኛለሁ፤ ሙሴ፦ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ ስለ ተከተልከው የረገጥከው ምድር ለአንተና ለልጆችህ የዘለዓለም ርስት ይሆናል’ ” ብሎ በዚያን ቀን በመሐላ ቃል ገብቶልኝ ነበር።
ኢያሱ 14:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ ጌታ በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ። የጌታ ባርያ ሙሴ ምድሪቱን እንድሰልል ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ጎልማሳ ነበርሁ እኔም ተመልሼ በልቤ የነበረውን ቃል ተናገርሁ። ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ፤ እኔ ግን አምላኬን ጌታን ፈጽሜ ተከተልሁ። ሙሴም በዚያ ቀን እንዲህ ብሎ ማለ፦ ‘አምላኬን ጌታን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም በእርግጥ ርስት ይሆናል።’