መጽሐፈ ኢያሱ 14:6-9

መጽሐፈ ኢያሱ 14:6-9 መቅካእኤ

የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ ጌታ በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ። የጌታ ባርያ ሙሴ ምድሪቱን እንድሰልል ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ጎልማሳ ነበርሁ እኔም ተመልሼ በልቤ የነበረውን ቃል ተናገርሁ። ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ፤ እኔ ግን አምላኬን ጌታን ፈጽሜ ተከተልሁ። ሙሴም በዚያ ቀን እንዲህ ብሎ ማለ፦ ‘አምላኬን ጌታን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም በእርግጥ ርስት ይሆናል።’