መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 14:6-9

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 14:6-9 አማ2000

የይ​ሁ​ዳም ልጆች በጌ​ል​ገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔ​ዛ​ዊ​ውም የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአ​ም​ላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃ​ዴስ በርኔ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታው​ቃ​ለህ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ምድ​ርን እሰ​ልል ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ከኝ ጊዜ እኔ የአ​ርባ ዓመት ሰው ነበ​ርሁ፤ እኔም በልቡ የነ​በ​ረ​ውን ቃል መለ​ስ​ሁ​ለት። ከእኔ ጋር የወጡ ወን​ድ​ሞች ግን የሕ​ዝ​ቡን ልብ አስ​ካዱ፤ እኔ ግን አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሜ እከ​ተ​ለው ዘንድ ተመ​ለ​ስሁ። ሙሴም በዚያ ቀን፦ ‘አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽ​መህ ተከ​ት​ለ​ሃ​ልና እግ​ርህ የረ​ገ​ጠው ምድር ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በር​ግጥ ርስት ይሆ​ናል’ ብሎ ማለ።