ዘፍጥረት 33:1-9

ዘፍጥረት 33:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ያዕ​ቆ​ብም ዐይ​ኑን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ዔሳ​ውን ሲመጣ አየው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆ​ቹ​ንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለ​ቱም ዕቁ​ባ​ቶቹ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ዕቁ​ባ​ቶ​ቹ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊት አደ​ረገ፤ ልያ​ንና ልጆ​ች​ዋን በኋላ፥ ራሔ​ል​ንና ዮሴ​ፍ​ንም ከሁሉ በኋላ አደ​ረገ። እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው አለፈ፤ ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳ​ውም እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ። ዔሳ​ውም ሊገ​ና​ኘው ሮጠ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አቅፎ ሳመው፤ ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት አለ​ቀሱ። ዔሳ​ውም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ሴቶ​ች​ንና ልጆ​ችን አየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለ። ዕቁ​ባ​ቶ​ቹም ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር ቀር​በው ሰገዱ፤ ደግ​ሞም ልያና ልጆ​ችዋ ቀር​በው ሰገ​ዱ​ለት፤ ከዚ​ያም በኋላ ዮሴ​ፍና ራሔል ቀር​በው ሰገዱ። ዔሳ​ውም፥ “ያገ​ኘ​ሁት ይህ ሠራ​ዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “በጌ​ታዬ ፊት ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ ነው” አለ። ዔሳ​ውም፥ “ለእኔ ብዙ አለኝ፤ ወን​ድሜ ሆይ፥ የአ​ንተ ለአ​ንተ ይሁን” አለ።

ዘፍጥረት 33:1-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ያዕቆብ አሻግሮ ተመለከተ፤ እነሆ ዔሳው አራት መቶ ሰዎች አስከትሎ እየመጣ ነበር። ስለዚህ ልጆቹን ለልያ፣ ለራሔልና ለሁለቱ አገልጋዮች አከፋፈላቸው። ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ። እርሱ ራሱም ቀድሟቸው ሄደ፤ ወንድሙም ዘንድ እስኪደርስ ድረስ ሰባት ጊዜ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጦ ሄዶ ዐቀፈው፤ በዐንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን አየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ ዐብረውህ ያሉት እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሴት አገልጋዮችና ልጆቻቸው ቀርበው እጅ ነሡ፤ ከዚያም ልያና ልጆቿ መጥተው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል መጡ፤ እነርሱም ቀርበው እጅ ነሡ። ዔሳውም፣ “ወደ እኔ ተነድቶ የመጣው ይህ ሁሉ መንጋ ምንድን ነው?” አለው። እርሱም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው። ዔሳው ግን፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እኔ በቂ አለኝ፤ የራስህን ለራስህ አድርገው” አለው።

ዘፍጥረት 33:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ እነሆም ዔሳውን ሲመጣ አየው ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም ባሪያዎች አደረጋቸው፤ ባሪያዎችንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ ልያንና ልጆችዋንም በኋለኛው ስፍራ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኍላ አደረገ። እርሱም በፊታቸው አለፈ ወደ ወንድሙም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ። ዔሳውም ሊገናኘው ሮጠ አንገቱንም አቅፎ ሳመው ተላቀሱም። ዓይኑንም አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ እንዲህም አለ፦ እነዚህ ምኖችህ ናቸው? እርሱም፦ እግዚአብሔር ለእኔ ለባሪያህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው አለ። ሴቶች ባሪያዎችም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው ሰገዱ ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀረበው ሰገዱ ከዚይም በኍላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ። እርሱም፦ ያገኘሁት ይህ ሠራዊት ሁሉ ምንህ ነው? አለ። እርሱም፦ በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ነው አለ። ዔሳውም፦ ለእኔ ብዙ አለኝ ወንድሜ ሆይ የአንተ ለአንተ ይሁን አለ።

ዘፍጥረት 33:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ያዕቆብ ቀና ብሎ ሲመለከት፥ ዔሳው አራት መቶ ሰዎችን አስከትሎ ሲመጣ አየ፤ ያዕቆብም ልጆቹን ከልያ፥ ከራሔልና ከሁለቱ ሴቶች አገልጋዮቹ ጋር ከፋፈላቸው። በመጀመሪያ ሁለቱን ሴቶች አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውን አስቀደመ፤ ቀጥሎ ልያንና ልጆችዋን አስከተለ፤ በመጨረሻም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ። ያዕቆብ ከሁሉ ቀድሞ ተጓዘ፤ ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው ሲቀርብ ወደ መሬት በመጐንበስ ሰባት ጊዜ እጅ ነሣ፤ ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጠ፤ በአንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ዕቅፍ አድርጎ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። ዔሳው በዙሪያው ተመልክቶ ሴቶቹንና ልጆቹን ባየ ጊዜ “እነዚህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች የማን ናቸው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ሲል መለሰ። ከዚህ በኋላ ሴቶች አገልጋዮቹ ከልጆቻቸው ጋር መጥተው እጅ ነሡ። ቀጥሎም ልያና ልጆችዋ ቀርበው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል ቀርበው እጅ ነሡ። ዔሳውም “እፊት እፊትስ እየተነዳ ሲሄድ ያየሁት የእንስሶች መንጋ ምንድን ነው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እርሱ በአንተ ፊት ሞገስ እንዳገኝ የላክሁልህ ነው” አለ። ዔሳውም “ወንድሜ ሆይ፥ እኔ በቂ ሀብት አለኝ፤ የአንተ ለራስህ ይሁን” አለው።

ዘፍጥረት 33:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ ተመለከተም፥ እነሆም ዔሳው እየመጣ ነበር፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ። ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም አገልጋዮች አደረጋቸው። ሴት አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውንም ከፊት አደረገ፥ ልያንና ልጆችዋንም አስከተለ፥ ከዚያም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ። እርሱም ከፊታቸው ቀደመ፥ ወደ ወንድሙም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ። ዔሳውም ሊገናኘው ሮጦ ተጠመጠመበት፥ አንገቱንም አቅፎ ሳመው፥ ተላቀሱም። ዓይኑን አንስቶም ሴቶችንና ልጆችን ባየ ጊዜ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” አለ። እርሱም፦ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ። ከዚህ በኋላ ሴቶች ባርያዎችም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው እጅ ነሡ፥ ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀረበው እጅ ነሡ፥ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል ቀርበው እጅ ነሡ። እርሱም፥ “ያገኘሁት ይህ ሁሉ ጓዝ ምንህ ነው?” አለ። እርሱም፥ “በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ነው” አለ። ዔሳውም፥ “ለእኔ ብዙ አለኝ፥ ወንድሜ ሆይ፥ የአንተ ለአንተ ይሁን አለ።”