ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 33:1-9

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 33:1-9 አማ2000

ያዕ​ቆ​ብም ዐይ​ኑን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ዔሳ​ውን ሲመጣ አየው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆ​ቹ​ንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለ​ቱም ዕቁ​ባ​ቶቹ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ዕቁ​ባ​ቶ​ቹ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊት አደ​ረገ፤ ልያ​ንና ልጆ​ች​ዋን በኋላ፥ ራሔ​ል​ንና ዮሴ​ፍ​ንም ከሁሉ በኋላ አደ​ረገ። እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው አለፈ፤ ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳ​ውም እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ። ዔሳ​ውም ሊገ​ና​ኘው ሮጠ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አቅፎ ሳመው፤ ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት አለ​ቀሱ። ዔሳ​ውም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ሴቶ​ች​ንና ልጆ​ችን አየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለ። ዕቁ​ባ​ቶ​ቹም ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር ቀር​በው ሰገዱ፤ ደግ​ሞም ልያና ልጆ​ችዋ ቀር​በው ሰገ​ዱ​ለት፤ ከዚ​ያም በኋላ ዮሴ​ፍና ራሔል ቀር​በው ሰገዱ። ዔሳ​ውም፥ “ያገ​ኘ​ሁት ይህ ሠራ​ዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “በጌ​ታዬ ፊት ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ ነው” አለ። ዔሳ​ውም፥ “ለእኔ ብዙ አለኝ፤ ወን​ድሜ ሆይ፥ የአ​ንተ ለአ​ንተ ይሁን” አለ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}