ዘፍጥረት 22:1-24

ዘፍጥረት 22:1-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በኋላ እን​ዲህ ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን ፈተ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም ሆይ፥” እር​ሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ። “የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አንድ ልጅ​ህን ይስ​ሐ​ቅን ይዘህ ወደ ከፍ​ተ​ኛው ተራራ ሂድ፤ እኔም በም​ነ​ግ​ርህ በአ​ንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ሠዋው” አለው። አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ። አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ቦታ​ውን ከሩቅ አየ። አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ዎ​ቹን አላ​ቸው፥ “አህ​ያ​ውን ይዛ​ችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደ​ዚያ ተራራ ሄደን እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ ሰግ​ደ​ንም ወደ እና​ንተ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።” አብ​ር​ሃ​ምም የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ዕን​ጨት አን​ሥቶ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ አሸ​ከ​መው፤ እር​ሱም እሳ​ቱ​ንና ቢላ​ዋ​ዉን በእጁ ያዘ፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ። ይስ​ሐ​ቅም አባ​ቱን አብ​ር​ሃ​ምን ተና​ገ​ረው፥ “አባቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “ልጄ፥ ምን​ድን ነው?” አለው። “እሳ​ቱና ዕን​ጨቱ ይኸው አለ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕቱ በግ ግን ወዴት አለ?” አለው። አብ​ር​ሃ​ምም፥ “ልጄ ሆይ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን በግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ጋ​ጃል” አለው፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​ውም ወደ​ዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዚያ መሠ​ዊ​ያ​ዉን ሠራ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ረበ​ረበ፤ ልጁን ይስ​ሐ​ቅ​ንም አስሮ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ በዕ​ን​ጨቱ ላይ በልቡ አስ​ተ​ኛው። አብ​ር​ሃ​ምም እጁን ዘረጋ፤ ልጁ​ንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ጠራና፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ። እር​ሱም፥ “በብ​ላ​ቴ​ናው ላይ እጅ​ህን አት​ዘ​ርጋ፤ አን​ዳ​ችም አታ​ድ​ር​ግ​በት፤ ለም​ት​ው​ድ​ደው ልጅህ ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ለ​ት​ምና አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ እን​ደ​ሆ​ንህ አሁን ዐው​ቄ​አ​ለሁ” አለው። አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኖ​ቹን አቅ​ንቶ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ፥ በኋ​ላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀን​ዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ሄዶ በጉን ወሰ​ደው፤ በልጁ በይ​ስ​ሐቅ ፈን​ታም ሠዋው። አብ​ር​ሃ​ምም ዛሬ በዚህ ተራራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ታየኝ ሲል ያን ቦታ “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ከሰ​ማይ ሁለ​ተኛ ጊዜ ጠራው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ለም​ት​ወ​ድ​ደው ልጅ​ህም ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ምና መባ​ረ​ክን እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤ የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉም በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤ ቃሌን ሰም​ተ​ሃ​ልና።” አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ብላ​ቴ​ኖቹ ተመ​ለሰ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ አብ​ረው ሄዱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ ተቀ​መጠ። እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ ለአ​ብ​ር​ሃም እን​ዲህ ተብሎ ተነ​ገረ፥ “እነሆ፥ ሚልካ ደግሞ ለወ​ን​ድ​ምህ ለና​ኮር ልጆ​ችን ወለ​ደች፤ እነ​ር​ሱም በኵሩ ዑፅ፥ ወን​ድሙ በዋ​ክሲ፤ የአ​ራም አባት ቀማ​ኤል፥ አኮ​ዛት፥ ኤዝ​ራው፥ ፌል​ዳስ፥ ዮፋ​ትና ባቱ​ኤል” ናቸው። ባቱ​ኤ​ልም ርብ​ቃን ወለደ፤ ሚልካ ለአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም ለና​ኮር የወ​ለ​ደ​ች​ለት ስም​ንቱ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። ሬሕማ የሚ​ሉ​አት ዕቅ​ብቱ ደግሞ ጥባ​ህን፥ ቤካን፥ ጠኮ​ንና ሜካን ወለ​ደች።

ዘፍጥረት 22:1-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” አለው። እርሱም “አቤቱ አለሁ” አለ። እግዚአብሔርም፣ “የምትወድደውን አንዱን ልጅህን፣ ይሥሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው። በማግስቱም ጧት አብርሃም ማልዶ ተነሣ፤ አህያውን ጭኖ፣ ሁለት አገልጋዮቹንና ልጁን ይሥሐቅን ይዞ፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚበቃውን ዕንጨት ከቈረጠ በኋላ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጕዞውን ጀመረ፤ በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ቦታውን ከሩቅ ተመለከተ፤ አገልጋዮቹንም “እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቈዩን፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ሰግደን እንመለሳለን” አላቸው። አብርሃም ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን ዕንጨት ወስዶ፣ ልጁን ይሥሐቅን አሸከመው፤ እሳቱንና ቢላዋውንም ራሱ ያዘ። ሁለቱም ዐብረው ሄዱ። ይሥሐቅም አባቱን አብርሃምን፣ “አባቴ ሆይ” አለው። አብርሃምም፣ “እነሆኝ፤ አለሁ ልጄ” አለው። ይሥሐቅም፣ “እሳቱና ዕንጨቱ ይኸው፤ ነገር ግን የሚቃጠለው መሥዋዕት በግ የት አለ?” ብሎ ጠየቀ። አብርሃምም፣ “ልጄ ሆይ፤ ለሚቃጠለው መሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል” አለው። ሁለቱም ዐብረው ጕዟቸውን ቀጠሉ። እግዚአብሔር ወደ አመለከተው ቦታ እንደ ደረሱ፣ አብርሃም መሠዊያ ሠራ፤ በላዩም ላይ ዕንጨት ረበረበ፤ ልጁን ይሥሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ዕንጨት ላይ አጋደመው። ከዚያም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላዋውን አነሣ። የእግዚአብሔር መልአክ ግን ከሰማይ፣ “አብርሃም! አብርሃም!” ብሎ ጠራው። አብርሃምም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ። እርሱም፣ “እጅህን በብላቴናው ላይ አታሳርፍ፤ ምንም ጕዳት አታድርስበት፤ እነሆ፤ እግዚአብሔርን እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፤ ልጅህን፣ ያውም አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሣሣህምና” አለው። አብርሃም ቀና ብሎ ተመለከተ፤ በቍጥቋጦ መካከልም ቀንዶቹ የተጠላለፉ አንድ አውራ በግ ከበስተኋላው አየ፤ ወደዚያው ሄዶ በጉን አመጣና የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው። ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል። የእግዚአብሔርም መልአክ አብርሃምን ከሰማይ ዳግመኛ ጠራው፤ እንዲህም አለው፤ “እግዚአብሔርም በራሴ ማልሁ አለ፤ አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሣሣህምና፣ በርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት፣ እንደ ባሕር ዳር አሸዋም አበዛዋለሁ። ዘሮችህም የጠላቶቻቸውን ደጆች ይወርሳሉ፤ አሕዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤ ቃሌን ሰምተሃልና።” ከዚያም አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰ፤ ተያይዘውም ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ኖረ። ከዚህ በኋላ እንዲህ ተብሎ ለአብርሃም ተነገረው፤ “ሚልካም ደግሞ የልጆች እናት ሆናለች፤ ለወንድምህም ለናኮር ወንዶች ልጆችን ወልዳለች። እነርሱም የበኵር ልጁ ዑፅና ወንድሙ ቡዝ፣ የአራም አባት ቀሙኤል፣ ኮዛት፣ ሐዞ፣ ፊልዳሥ፣ የድላፍና ባቱኤል ናቸው።” ባቱኤልም ርብቃን ወለደ። ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር የወለደችለት እነዚህ ስምንት ወንዶች ልጆች ናቸው። ከእነዚህም ሌላ የናኮር ቁባት ሬናሕ ደግሞ ጥባሕ፣ ገአም፣ ተሐሽና ሞክሳ የተባሉ ወንዶች ልጆች ወለደችለት።

ዘፍጥረት 22:1-24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከእነዚም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብረሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው፦ አብረሃም ሆይ። አብረሃምም፦ እንሆ፥ አለሁ አለ። የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሕቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መስዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ። አብረሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፥ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሕቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፥ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ። በሦስተኛውም ቀን አብርሃም ዓይኑን አነሣና ቦታውን ከሩቅ አየ። አብርሃምም ሎሌዎቹን አላቸው፦ አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን፥ ወደ እናንተም እንመለሳለን። አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ሁለቱም አብረው ሄዱ። ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው፦ አባቴ ሆይ አለ። እርሱም፦ እነሆኝ ልጄ አለው። እሳቱና እንጨቱ ይኸው አለ፤ የመስዋዓቱ በግ ግን ወዴት ነው? አለ። አብርሃምም፦ ልጄ ሆይ፥ የመስዋዕቱን በግ እግዚአብሐር ያዘጋጃል አለው፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ። እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሰዊያውን ሰራ፥ እንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሰዊያው በእንጨቱ ላይ አጋደመው። አብርሃምም እጁን ዘረጋ፥ ልጁንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ። የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና፦ አብርሃም አብርሃም አለው፤ እርሱ፦ እነሆኝ አለ። እርሱም፦ በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ አንዳችም አታድርግበት፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምን እግዚአብሔር የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለ። አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር አዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው፦ በልጁም ፋንታ መሥውዕት አድርጎ ሠዋው። አብርሃምም ያንን ቦታ ያህዌ ይርኤ ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም፤ እስከ ዛሬም ድረስ በእግዚአብሔር ተራራ ይታያል ይባላል። የእግዚአብሔር መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለትኛ ጊዜ ጠራው፦ እንዲህም አለው፦ እንዴህም አለው፦ እግዜአብሔር፦ በራሴማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፦ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምን በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፦ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር እንዳል አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካል፦ ቃሌን ሰምተሃልና። አብርሃምም ወደ ብላቴኖቹ ተመለሰ፦ ተነሥተውም ወደ ቤርሳቤህ አብረው ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ። ይህም ከሆነ በኋል አብርሃም እንዲህ ተብሎ ተነገር፦ እነሆ፦ ሚልካ ደግሞ ለወለድምህ ለናኮር ልጆችን ወሰደች፤ እነርሱም በኵሩ ዐፅ፥ ወንድሙ ቡዝ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፥ ኮዛት፥ ሐዞ፥ ፊልዳሥ፥ የድላ፥ ባቱኤል ናቸው። ባቱኤልም ርብቃን ወለድ፤ እነዚህን ስምንቱን ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር ወለደች። ሬሕማ የሚሉአት ቁባቱ ደግሞ ጥባህን፥ ገአምን፥ ተሐሸን፥ ሞክሳን ወለደች።

ዘፍጥረት 22:1-24 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ። እግዚአብሔርም “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው። አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ። በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ። ከዚህ በኋላ አብርሃም አገልጋዮቹን “እናንተ ከአህያው ጋር እዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ከሰገድን በኋላ እንመለሳለን” አላቸው። አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢለዋውንና እሳቱን ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሲሄዱ ሳለ፥ ይስሐቅ አብርሃምን “አባባ!” አለው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁ ልጄ!” አለው። ይስሐቅም “እነሆ፥ እሳትና እንጨት ይዘናል፤ ታዲያ ለመሥዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?” በማለት አብርሃምን ጠየቀው። አብርሃምም “ልጄ ሆይ፥ ለመሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ለራሱ ያዘጋጃል” አለው፤ ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ። እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠርቶ እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሠዊያው ላይ አጋደመው። ልጁን ለማረድ ቢላዋ አንሥቶ እጁን ዘረጋ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ “አብርሃም! አብርሃም!” ብሎ ጠራው። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ። መልአኩም “ልጁን አትንካ፤ ምንም ዐይነት ጒዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት ስለ አልተቈጠብክ እነሆ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቼአለሁ።” አብርሃም ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ ቀንዶቹ በቊጥቋጦ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። አብርሃም ያንን ቦታ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ሰየመው፤ ዛሬም ቢሆን ሰዎች “እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል” ይላሉ። የእግዚአብሔር መልአክ ሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ጠራውና እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ‘ብዙ በረከት እንደምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ’ ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቈጠብክ፥ እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነሥተው ከተሞቻቸውን ይይዛሉ። ትእዛዜን ስለ ፈጸምክ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።” ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰና በአንድነት ሆነው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ። ከዚህ ሁሉ በኋላ ሚልካ ለወንድሙ ለናኮር ልጆች እንደ ወለደችለት አብርሃም ሰማ፤ እነርሱም፥ የመጀመሪያው ዑፅ፥ ወንድሙም ቡዝ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፤ ኬሠድ፥ ሐዞ፥ ፊልዳሽ፥ ይድላፍና በቱኤል ናቸው። በቱኤል ርብቃን ወለደ፤ ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለናኮር ወለደችለት። ረኡማ የተባለችው የናኮር ቊባት ደግሞ ጤባሕን፥ ገሐምን፥ ተሐሽንና፥ ማዕካን ወለደችለት።

ዘፍጥረት 22:1-24 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም፥ “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ። እግዚአብሔርም፥ “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሕቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፥ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋልኝ” አለው። በማግስቱም ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕት የሚሆን ዕንጨትን ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፥ ከእርሱም ጋር ሁለቱን አገልጋዮቹን እና ልጁን ይስሕቅን ይዞ፥ እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ተነሥቶ ጉዞ ጀመረ። በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ። ከዚህ በኋላ አብርሃምም አገልጋዮቹን፥ “አህያውን ይዛችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ተራራ ሄደን እንሰግዳለን፤ ሰግደንም ወደ እናንተ እንመለሳለን” አላቸው። አብርሃምም የመሥዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፥ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ከዚያም ሁለቱ አብረው ሄዱ። ይስሐቅ አብርሃምን “አባቴ ሆይ!” አለው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁ ልጄ!” አለው። ይስሐቅም “እነሆ፥ እሳትና እንጨት ይዘናል፤ ነገር ግን ለመሥዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?” በማለት ጠየቀው። አብርሃምም “ልጄ ሆይ፥ ለመሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ራሱ ያዘጋጃል” አለው፤ ከዚያም ሁለቱ አብረው ሄዱ። እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠራና እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ላይ፥ ከእንጨቱ በላይ አጋደመው። እጁንም ዘርግቶ፥ ልጁን ለማረድ አብርሃም ቢላዋ አነሣ። ነገር ግን የጌታ መልአክ “አብርሃም! አብርሃም!” ሲል ከሰማይ ተጣራ። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ። እርሱም “በልጁ ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ ምንም ዓይነት ጉዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ለመስጠት እንዳልሳሳህ እነሆ አየሁ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን አውቄአለሁ” አለ። አብርሃምም ዓይኑን አንስቶ ሲመለከት፥ ከኋላው እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዛፍ ቊጥቋጦ ተይዞ አየ፥ አብርሃምም ሄዶ በጉን አመጣና፥ በልጁ ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። ስለዚህም አብርሃም ያንን ቦታ “ጌታ ያዘጋጃል (ያህዌ ይርኤ)” ብሎ ሰየመው፤ ዛሬም ቢሆን ሰዎች “ጌታ በተራራው ላይ ያዘጋጃል” ይላሉ። የጌታ መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው፥ እንዲህም አለው፦ “ጌታ፥ በራሴ እምላለሁ፥ ይላል፤ ምክንያቱም ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልከኝምና፤ በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና፥ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ።” ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰ፥ ተነሥተውም ወደ ቤርሳቤህ አብረው ሄዱ፥ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ። ይህም ከሆነ በኋላ ለአብርሃም እንዲህ ተብሎ ተነገረ፦ “እነሆ፥ ሚልካ ደግሞ ለወንድምህ ለናኮር ልጆችን ወለደች፤ እነርሱም የመጀመሪያው ዑፅ፥ ወንድሙም ቡዝ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፤ ኬሠድ፥ ሐዞ፥ ፊልዳሽ፥ ይድላፍና በቱኤል ናቸው።” በቱኤል ርብቃን ወለደ፤ ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለናኮር ወለደችለት። እንዲሁም፥ ረኡማ የተባለችው የናኮር ቊባት ደግሞ ጤባሕን፥ ገሐምን፥ ተሐሽንና፥ ማዕካን ወለደችለት።