የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፥ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው። የምድያምም እጅ በእስራኤል ላይ ጠነከረች፥ ከምድያምም የተነሣ የእስራኤል ልጆች በተራራ ላይ ጉድጓድና ዋሻ ምሽግም አበጁ። እስራኤልም ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያን አማሌቃውያንም በምሥራቅም የሚኖሩ ሰዎች ይመጡባቸው ነበር፥ በእነርሱም ላይ ይሰፍሩ ነበር፥ እስከ ጋዛም ድረስ የምድሩን ቡቃያ ያጠፉ ነበር፥ ምግብንም ለእስራኤል አይተዉም ነበር፥ በግ ወይም በሬ ወይም አህያ ቢሆን አይተዉም። እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው በብዛት እንደ አንበጣ ሆነው ይመጡ ነበር፥ ለእነርሱና ለግመሎቻቸውም ቁጥር አልነበራቸውም፥ ምድሪቱንም ያጠፉ ዘንድ ይመጡ ነበር። ከምድያምም የተነሣ እስራኤል እጅግ ተጠቁ፥ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
መጽሐፈ መሳፍንት 6 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መሳፍንት 6:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች