መጽሐፈ መሳፍንት 6:1-6

መጽሐፈ መሳፍንት 6:1-6 አማ05

የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንደገና በደሉ፤ እግዚአብሔርም ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰባት ዓመት ሙሉ ገዙአቸው፤ የምድያማውያን ኀይል በእስራኤል ላይ በረታ፤ በእነርሱም ምክንያት የእስራኤል ሕዝብ መሸሸጊያ ቦታ፥ ዋሻና ምሽግ አዘጋጁ። እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ምድያማውያን፥ ከዐማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች እየመጡ አደጋ ይጥሉባቸው ነበር። በአገሪቱ ላይ በመስፈር በጋዛ ዙሪያ እስካለው ስፍራ ድረስ የምድሪቱን ሰብል ያጠፉ ነበር፤ የበግ፥ የከብትና የአህያ መንጋቸውንም እየነዱ ስለሚወስዱባቸው ለእስራኤላውያን ምንም ነገር አያስቀሩላቸውም ነበር። ከከብቶቻቸውና ከድንኳኖቻቸው ጋር ሲመጡ ያንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ እነርሱንና ግመሎቻቸውን ለመቊጠር እስከማይቻል ድረስ እጅግ ብዙዎች ነበሩ፤ መጥተውም ምድሪቱን ያጠፉ ነበር። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድያማውያን ምክንያት ችግር ደረሰባቸው፤ እንዲረዳቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።