ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፥ ይሁዳም ከታመነው ቅዱሱ ከእግዚአብሔር ጋር አይጸናም። ኤፍሬም ነፋስን ይበላል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል፥ ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፥ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ። እግዚአብሔርም ደግሞ ከይሁዳ ጋር ክርክር አለው፥ ያዕቆብንም እንደ መንገዱ ይቀጣል፥ እንደ ሥራውም ይመልስለታል። በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ፥ ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፥ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም ከእኛ ጋር ተነጋገረ። እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፥ የመታሰቢያው ስም እግዚአብሔር ነው።
ትንቢተ ሆሴዕ 12 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ሆሴዕ 12:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች