ሆሴዕ 12:1-6

ሆሴዕ 12:1-6 NASV

ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋራ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ የወይራ ዘይትንም ወደ ግብጽ ይልካል። እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል። በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋራ ታገለ። ከመልአኩም ጋራ ታገለ፤ አሸነፈውም፤ በፊቱ ሞገስን ለማግኘት አልቅሶ ለመነው፣ እርሱንም በቤቴል አገኘው፤ በዚያም ከርሱ ጋራ ተነጋገረ፤ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር፣ የሚታወቅበት ስሙ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።