ሆሴዕ 12:1-6

ሆሴዕ 12:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ኤፍ​ሬም በሐ​ሰት፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ይሁ​ዳም በተ​ን​ኰል ከበ​ቡኝ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐወ​ቃ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ። ኤፍ​ሬም ግን ክብ​ር​ንና ከንቱ ነገ​ርን የሚ​ያ​ሳ​ድድ ክፉ ጋኔን ነው። ሁል​ጊ​ዜም ሐሰ​ት​ንና ተን​ኰ​ልን ያበ​ዛል፤ ከአ​ሦ​ርም ጋር ቃል ኪዳን ያደ​ር​ጋል፤ ምሕ​ረ​ትም ያደ​ር​ጉ​ለት ዘንድ ወደ ግብፅ ዘይ​ትን ይል​ካል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከይ​ሁዳ ጋር ይዋ​ቀ​ሳል፤ ያዕ​ቆ​ብ​ንም እንደ መን​ገዱ ይበ​ቀ​ለ​ዋል፤ እንደ ሥራ​ውም ይከ​ፍ​ለ​ዋል። በማ​ኅ​ፀን ውስጥ ወን​ድ​ሙን በተ​ረ​ከዙ ያዘው፤ በደ​ካ​ማ​ነ​ቱም ጊዜ ከአ​ም​ላክ ጋር ታገለ። ከመ​ል​አ​ኩም ጋር ታግሎ አሸ​ነፈ፤ አል​ቅ​ሶም ለመ​ነኝ። በቤ​ት​አ​ዎ​ንም አገ​ኘኝ፤ በዚ​ያም ከእኔ ጋር ተነ​ጋ​ገረ። ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ሰ​ቢ​ያው ነው።