ትንቢተ ዕንባቆም 1:1-4

ትንቢተ ዕንባቆም 1:1-4 አማ54

ነቢዩ ዕንባቆም ያየው ሸክም ይህ ነው። አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም። በደልንስ ስለ ምን አሳየኸኝ? ጠማምነትንስ ስለ ምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፥ ጠብና ክርክር ይነሣሉ። ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፥ ፍርድም ድል ነሥቶ አይወጣም፥ ኃጢአተኛ ጻድቅን ይከብባልና፥ ስለዚህ ፍርድ ጠማማ ሆኖ ይወጣል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}