ዕንባቆም 1:1-4
ዕንባቆም 1:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነቢዩ ዕንባቆም ያየው ሸክም ይህ ነው። አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም። በደልንስ ስለ ምን አሳየኸኝ? ጠማምነትንስ ስለ ምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፣ ጠብና ክርክር ይነሣሉ። ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፥ ፍርድም ድል ነሥቶ አይወጣም፣ ኃጢአተኛ ጻድቅን ይከብባልና፣ ስለዚህ ፍርድ ጠማማ ሆኖ ይወጣል።
ዕንባቆም 1:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነቢዩ ዕንባቆም የተቀበለው ንግር፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለርዳታ እየተጣራሁ፣ አንተ የማትሰማው፣ “ግፍ በዛ” ብዬ እየጮኽሁ፣ አንተ የማታድነው እስከ መቼ ነው? ስለ ምን በደልን እንዳይ አደረግኸኝ? እንዴትስ ግፍ ሲፈጸም ትታገሣለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ አለ፤ ጠብና ግጭት በዝቷል። ስለዚህ ሕግ ደክሟል፤ ፍትሕ ድል አይነሣም፤ ፍትሕ ይጣመም ዘንድ፣ ክፉዎች ጻድቃንን ይከብባሉ።
ዕንባቆም 1:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነቢዩ ዕንባቆም ያየው ሸክም ይህ ነው። አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም። በደልንስ ስለ ምን አሳየኸኝ? ጠማምነትንስ ስለ ምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፥ ጠብና ክርክር ይነሣሉ። ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፥ ፍርድም ድል ነሥቶ አይወጣም፥ ኃጢአተኛ ጻድቅን ይከብባልና፥ ስለዚህ ፍርድ ጠማማ ሆኖ ይወጣል።
ዕንባቆም 1:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ለነቢዩ ለዕንባቆም በራእይ የገለጠለት ቃል የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔር ሆይ! ርዳታህን በመጠየቅና በእኛ ላይ የደረሰውን ዐመፅ በመግለጥ ወደ አንተ ስንጮህ የምታዳምጠንና የምታድነን መቼ ነው? ለምን ይህ ሁሉ ግፍ ሲደርስ እንዳይ አደረግኸኝ? አንተስ ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታለህ? ጥፋትንና ዐመፅን አያለሁ፤ ጠብና ክርክርም ይነሣሉ። በዚህ መሠረት ሕግ ላልቶአል፤ ፍትሕም ተዛብቶአል፤ ክፉዎች በደጋግ ሰዎች ላይ ከበባ አድርገዋል፤ ስለዚህ ፍርድ ተጣሟል።