ኦሪት ዘፍጥረት 41:46-49

ኦሪት ዘፍጥረት 41:46-49 አማ54

ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ። በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን ዓመታ እህል ሁሉ ሰበሰበ እህልንም በከተማቹ አደለበ፤ በየከተማይቱ ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ። ዮሴፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስንዴን አከማቸ መሰፈርን እስኪተው ድረስ ሊሰፈር አልተቻለምና።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}