ዘፍጥረት 41:46-49
ዘፍጥረት 41:46-49 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ግብፅ ያስገኘችው እህል ሁሉ ክምር ሆነ። በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን የጥጋብ ዓመታት እህል ሁሉ ሰበሰበ፤ እህልንም በከተሞቹ አደለበ፤ በየከተማይቱም ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ። ዮሴፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስንዴን አከማቸ፤ መስፈር እስኪሳናቸው ድረስ፤ ሊሰፈር አልተቻለምና።
ዘፍጥረት 41:46-49 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ። በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፣ ዮሴፍ በግብጽ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፤ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ። ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር።
ዘፍጥረት 41:46-49 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ። በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን ዓመታ እህል ሁሉ ሰበሰበ እህልንም በከተማቹ አደለበ፤ በየከተማይቱ ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ። ዮሴፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስንዴን አከማቸ መሰፈርን እስኪተው ድረስ ሊሰፈር አልተቻለምና።
ዘፍጥረት 41:46-49 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ዮሴፍ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ ዮሴፍ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ በመላው የግብጽ ምድር በመዘዋወር ጒብኝት ያደርግ ነበር፤ በሰባቱ የጥጋብ ዓመቶች ምድሪቱ እጅግ ብዙ ሰብል ሰጠች። በግብጽ አገር በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመቶች የተገኘውን ሰብል ሰብስቦ በየከተሞች አከማቸ፤ በየእያንዳንዱ ከተማ ያከማቸው እህል በዙሪያው ከሚገኙት እርሻዎች የተመረተ ነበር። በዚህ ዐይነት ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የሆነ እጅግ ብዙ እህል አከማቸ፤ እህሉ እጅግ ብዙ ከመሆኑ የተነሣ እየሰፈረ መጠኑን ለማወቅ የነበረውን ዕቅድ ተወ።
ዘፍጥረት 41:46-49 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ። በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፥ ዮሴፍ በግብጽ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፤ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ። ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር።