ኦሪት ዘፍጥረት 33:1-9

ኦሪት ዘፍጥረት 33:1-9 አማ54

ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ እነሆም ዔሳውን ሲመጣ አየው ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም ባሪያዎች አደረጋቸው፤ ባሪያዎችንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ ልያንና ልጆችዋንም በኋለኛው ስፍራ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኍላ አደረገ። እርሱም በፊታቸው አለፈ ወደ ወንድሙም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ። ዔሳውም ሊገናኘው ሮጠ አንገቱንም አቅፎ ሳመው ተላቀሱም። ዓይኑንም አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ እንዲህም አለ፦ እነዚህ ምኖችህ ናቸው? እርሱም፦ እግዚአብሔር ለእኔ ለባሪያህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው አለ። ሴቶች ባሪያዎችም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው ሰገዱ ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀረበው ሰገዱ ከዚይም በኍላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ። እርሱም፦ ያገኘሁት ይህ ሠራዊት ሁሉ ምንህ ነው? አለ። እርሱም፦ በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ነው አለ። ዔሳውም፦ ለእኔ ብዙ አለኝ ወንድሜ ሆይ የአንተ ለአንተ ይሁን አለ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}