ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 14:1-4

ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 14:1-4 አማ54

የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ የንጉሡ ልብ ወደ አቤሴሎም እንዳዘነበለ አወቀ። ኢዮአብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብልሃተኛ ሴት አስመጣና፦ አልቅሺ፥ የኅዘንም ልብስ ልበሺ፥ ዘይትም አትቀቢ፥ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እንደምታለቅሺ ሁኚ፥ ወደ ንጉሡም ገብተሽ እንዲህ ያለውን ቃል ንገሪው አላት፥ ኢዮአብም ቃሉን በእርስዋ አፍ አደረገ። እንዲሁም የቴቁሔይቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግምባርዋ በምድር ላይ ወደቀች፥ እጅ ነሥታም፦ ንጉሥ ሆይ፥ አድነኝ አለች።