መጽሐፈ ጥበብ 11
11
ጥበብ የእስራኤልን ሕዝብ በበርሃ እንደ መራቻቸው
1እርስዋ በቅዱሱ ነቢይ እጅ ሥራቸውን አቃናች፤ 2ማንም ወዳልኖረበት ምድረ በዳም ሄደው ኖሩ። ባልተረገጠች ቦታም የድንኳኖቻቸውን ካስማ ተከሉ። 3ተዋጊዎችንም ተቋቋሟቸው፤ ጠላቶችንም ተበቀሏቸው። 4በተጠሙ ጊዜም ጠሩህ፥ ከዐለት ድንጋይም ውኃ ተሰጣቸው። ከጽኑ ድንጋይም ለጥማቸው ፈውስ ተሰጣቸው። 5ጠላቶቻቸውም በዚህ ሥራ ተፈርዶባቸው ጠፉ። 6በዚህም ተቸግረው በተጨነቁ ጊዜ በጎ ነገርን አደረግህላቸው። 7በተገደሉት ሰዎች ደም እነዚያ ባደፈረሱት በማይጐድለው ወንዝ ምንጭ ፋንታ፥ 8ሕፃናት በዐዋጅ መገደላቸውን ለመዝለፍ በተስፋ ሳታስጠብቅ ፈጥነህ ያመነጨኸውን ብዙ ውኃ ሰጠኻቸው። 9እንደዚሁም በተጠሙ ጊዜ ስለተፈታተኑህ ተቃዋሚዎችን ፈረድህባቸው። 10እነርሱ ግን በምሕረትህ ተገሠጹ፥ ክፉዎችም በመዓት በተፈረደባቸው ጊዜ እንዴት እንደ ተቀጡ ዐወቁ። 11እነዚህንም እንደሚቀጣ አባት ገሠጽኻቸው። እነዚያን ግን ርኅራኄ እንደሌለው ንጉሥ ተከትለህ ቀጣኻቸው። 12በዚህም አምሳል ገረፍኻቸው። ሳሉም፥ ሳይኖሩም አሳዘንኻቸው። 13እጥፍ ኀዘን አግኝቶአቸዋልና፥ ያለፈውንም ክፉ ነገር የማሰብ ጩኸት አግኝትዋቸዋልና። 14በመከራቸውም በጎ ነገር እንዳደረገላቸው በሰሙ ጊዜ እነርሱ ከእግዚአብሔር የተገኘ ደስታ አደረጉት።
በኃጥኣን ላይ የሚደርስ ቅጣት
15ዳግመኛም በክፋት ቀድሞ የጣሉትን አጡት፤ ከዚህም በኋላ በመዘባበት ከእርሱ ሸሹ፤ ከትእዛዙ መውጣት ፍጻሜ የተነሣም አደነቁ፥ ጻድቃንም እንደ ተጠሙ እነርሱ የተጠሙ አይደሉም። 16አእምሮ በሌላት በልቡናቸው ክፋት በሳቱባት ጊዜ፥ የማይናገር፥ የተናቀና ከንቱ ሀብት እንስሳን አምልከዋልና፥ 17ሰው በበደለበት ሥራ እንዲፈረድበት ያውቁ ዘንድ ለመበቀል የማይናገር ብዙ እንስሳን ላክህባቸው። 18ዓለምን ካለመኖር ለፈጠረ ሁሉን ለሚችል ቀኝ እጅህ ብዙ ድቦችንና ቍጡ አንበሶችን ትልክባቸው ዘንድ አይሳነውምና። 19ያም ባይሆን ድንገት የተፈጠሩ የማይታወቁ፥ የሚያላልብና የሚፋጅ እሳትን የሚተነፍሱ፥ ያም ባይሆን የሚከረፋ የጢስ መዓዛን የሚተነፍሱ፥ ያም ባይሆን ከክፉ ዓይናቸው የእሳት ፍንጣሪን ቦግ ቦግ የሚያደርጉ ቍጣን የተሞሉ አውሬዎችን ላክህባቸው። 20ሊያጠፋቸው የሚችል ክፋታቸው ወይም ፍርዳቸው ብቻ አይደለም። ነገር ግን መልካቸው ባስፈራቸውና ባጠፋቸው ነበር።
እግዚአብሔር ኀያል መሓሪም ስለ መሆኑ
21ከዚህም በቀር፦ ስታባርራቸው፥ በኀይልህ መንፈስም ስታጠፋቸው፥ በአንዲት ምልክት ይጠፉ ዘንድ በተገባቸው ነበር። ነገር ግን ሁሉን በመጠን፥ በቍጥርና በሚዛን ሠራህ።
22የከሃሊነትህ ገናናነት በአንተ ዘንድ ሁልጊዜ ይኖራልና፥ የክንድህ ጽንዐት ኀይልንም ማን ይቃወማታል? 23ዓለሙ ሁሉ በፊትህ እንደ ሚዛን ውልብልቢት ነውና፥ በማለዳም በምድር ላይ እንደ ወረደች እንደ ጠል ጠብታ ነውና።
24አንተ ሁሉን የምትችል ነህና ሁሉን ይቅር ትላለህ፥ ለንስሓም እየጠበቅኸው የሰውን ኀጢአት ቸል ትላለህ። 25ያሉትን ሁሉ ትወዳለህ፥ ከፈጠርኸው ፍጥረትም ምንም የምትንቀው የለም፥ ብትጠላውስ ኖሮ አትፈጥረውም ነበርና። 26አንተ ካልወደድኸው በፊትህ እንደምን በጸና ነበር! አንተስ ካልጠራኸው እንደምን በተጠበቀ ነበር! 27ለፍጥረቱም ሁሉ ትራራለህ፥ ይቅርም ትላለህ። ሰውን የምትወድድ አቤቱ፥ ሁሉ ያንተ ነውና፥
Currently Selected:
መጽሐፈ ጥበብ 11: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ