መጽ​ሐፈ ጥበብ 12

12
1ጥፋት የሌ​ለ​በት ቸር መን​ፈ​ስህ በሁሉ አለና። 2ስለ​ዚ​ህም የተ​ሰ​ነ​ካ​ከ​ሉ​ትን ሰዎች ለፍ​ርድ እን​ዲ​መች ጥቂት በጥ​ቂት ትዘ​ል​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ የበ​ደ​ሉ​ት​ንም በደል ታሳ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ርቀው ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን በተ​ረዱ ጊዜ አቤቱ፥ ያም​ኑ​ብህ ዘንድ ትገ​ሥ​ጻ​ቸ​ዋ​ለህ።
ስለ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ኀጢ​አት
3በቅ​ድ​ስት ሀገ​ርህ የሚ​ኖ​ሩ​ትን የቀ​ደ​ሙ​ትን ሰዎች፥ 4ስለ ተጠላ የሟ​ርት ሥራ​ቸ​ውና ከጽ​ድቅ ስለ​ራቀ በዓ​ላ​ቸው፥ 5ያለ​ር​ኅ​ራ​ኄም ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ስለ​መ​ግ​ደ​ላ​ቸው፥ የሰ​ዎ​ችን ሆድ ዕቃና ሥጋ​ቸ​ውን ለመ​ብ​ላት፥ ደማ​ቸ​ው​ንም ለመ​ጠ​ጣት ስለ መፍ​ቀ​ዳ​ቸው ጠል​ተ​ኻ​ቸ​ዋል። የጌ​ት​ነ​ት​ህን ምሥ​ጢ​ራት ማወቅ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ርቋ​ልና። 6ከማ​ንም ዘንድ ረዳት የሌ​ላ​ቸው ሰዎ​ች​ንም ይገ​ድ​ላሉ፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም እጅ ታጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ወደ​ድህ። 7ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ከሀ​ገሩ ሁሉ በአ​ንተ ዘንድ የከ​በ​ረች ለእ​ነ​ርሱ የም​ት​ገባ ሀገ​ርን ይይዙ ዘንድ ነው። 8ነገር ግን ሰውን ይቅር እን​ደ​ም​ትል እነ​ር​ሱ​ንም ይቅር አል​ኻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም ጥቂት በጥ​ቂት እን​ዲ​ያ​ጠፉ ከሠ​ራ​ዊ​ትህ አስ​ቀ​ድሞ የት​ንኝ ወራ​ሪን ላክ​ህ​ባ​ቸው። 9ያም ባይ​ሆን በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ማ​ር​ኳ​ቸው ክፉ​ዎ​ችን በጻ​ድ​ቃን እጅ ትጥ​ላ​ቸው ዘንድ አይ​ሳ​ን​ህም ነበር፥ ያም ባይ​ሆን ለክ​ፉ​ዎች አው​ሬ​ዎች ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥ ያም ባይ​ሆን በአ​ንድ ቃል አዝ​ዘህ ታጠ​ፋ​ቸው ዘንድ አይ​ሳ​ን​ህም ነበር። 10ለእ​ነ​ዚህ የን​ስሓ ቦታ ሰጥ​ተህ ይህ ጥቂት በጥ​ቂት ይሆን ዘንድ ፈረ​ድህ፤ ይህ​ንም ማድ​ረ​ግህ አኗ​ኗ​ራ​ቸው ክፉ እንደ ሆነ፥ ክፋ​ታ​ቸ​ውም እጅግ እንደ በዛ፥ ዐሳ​ባ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ ሳታ​ውቅ አይ​ደ​ለም። 11ከጥ​ንት ጀምሮ የተ​ረ​ገሙ ዘሮች ናቸ​ውና፥ በበ​ደ​ሉ​በት በደል ዕድ​ሜን የም​ት​ሰ​ጣ​ቸው ማን​ንም አፍ​ረህ አይ​ደ​ለም።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሁሉ ገዥ ስለ መሆኑ
12“ምን አደ​ረ​ግህ?” የሚ​ልህ ማን ነው? ፍር​ድ​ህ​ንስ የሚ​ቃ​ወ​መው ማን ነው? ወይስ የሚ​ከ​ስህ ማን ነው? አንተ የፈ​ጠ​ር​ኻ​ቸው አሕ​ዛ​ብስ ስለ ጠፉ የሚ​መ​ራ​መ​ርህ ማን ነው? ስለ በደ​ለ​ኞች ሰዎ​ችም ለመ​ከ​ራ​ከር ወደ አንተ የሚ​ደ​ርስ ዳኛ ማን ነው? 13የፈ​ረ​ድህ በግፍ እን​ዳ​ይ​ደለ ትገ​ልጥ ዘንድ ስለ ሰው ሁሉ የሚ​ያ​ስብ ከአ​ንተ በቀር ሌላ አም​ላክ የለ​ምና። 14ንጉ​ሥም ቢሆን፥ መስ​ፍ​ንም ቢሆን ስለ ፈረ​ድ​ህ​ባ​ቸው ሰዎች አን​ተን እያማ ከአ​ንተ ጋር መተ​ያ​የት አይ​ች​ልም። 15አንተ ሁሉን በእ​ው​ነት የም​ታ​ዘ​ጋጅ እው​ነ​ተኛ ነህና ለፍ​ርድ የተ​ገባ ያይ​ደ​ለ​ውን ትፈ​ር​ድ​በት ዘንድ ከኀ​ይ​ልህ የተ​ነሣ ልዩ ሥራ ነው። 16ከሃ​ሊ​ነ​ትህ የጽ​ድቅ መጀ​መ​ሪያ ነውና፥ ሁሉን መፍ​ጠ​ር​ህና መግ​ዛ​ትህ ሁሉን ይቅር እን​ድ​ትል ያደ​ር​ግ​ሃል። 17የከ​ሃ​ሊ​ነ​ት​ህ​ንም ፍጻሜ በማ​ያ​ምን ኀይ​ል​ህን ገል​ጠ​ሃ​ልና የማ​ያ​ም​ኑ​ትን መደ​ፋ​ፈ​ራ​ቸ​ውን ትዘ​ል​ፋ​ለህ። 18አንተ ኀያል መኰ​ንን ስት​ሆን በቅ​ን​ነት ትፈ​ር​ዳ​ለህ። መቼም ቢሆን ከወ​ደ​ድህ ከሃ​ሊ​ነት በአ​ንተ ዘንድ አለና በብዙ ቸር​ነት ታኖ​ረ​ና​ለህ።
19እን​ዲህ ባለ ሥራም ጻድቅ ሰው ርኅ​ሩ​ኅና ሰው ወዳጅ መሆን ይገ​ባው ዘንድ ወገ​ኖ​ች​ህን አስ​ተ​ማ​ርህ፤ ለል​ጆ​ች​ህም በጎ ተስ​ፋን አደ​ረ​ግህ፥ አንተ ለበ​ደ​ለኛ ንስ​ሓን ትሰ​ጣ​ለ​ህና። 20ለሞት የሚ​ገቡ እነ​ዚህ የል​ጆ​ችህ ጠላ​ቶች ባሉ​በት ዘን​ድም በእ​ን​ዲህ ያለ ትዕ​ግ​ሥት ፈረ​ድህ፥ ከክ​ፉም ይድ​ኑ​ባት ዘንድ ዘመ​ን​ንና መን​ገ​ድን ሰጠ​ሃ​ቸው። 21ለበጎ ተስፋ መሓ​ላ​ንና ቃል ኪዳ​ንን ለሰ​ጠ​ሃ​ቸው ለል​ጆ​ችህ ምን ያህል ተጠ​ን​ቅ​ቀህ ትፈ​ር​ድ​ላ​ቸው ይሆን? 22ስለ​ዚ​ህም በፈ​ረ​ድ​ህ​ባ​ቸው ጊዜ ቸር​ነ​ት​ህን እና​ስብ ዘንድ፥ እኛን እየ​መ​ከ​ርህ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንን በብዙ ፍርድ ብዙ ጊዜ ትቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በፈ​ረ​ድ​ህ​ብ​ንም ጊዜ ይቅ​ር​ህ​ታን ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።
ስለ ግብ​ፃ​ው​ያን ቅጣት
23በዚህ ግን በስ​ን​ፍ​ናና በኀ​ጢ​አት የኖሩ በደ​ለ​ኞች ሰዎ​ችን ቀጣህ፥ በየ​ራ​ሳ​ቸ​ውም ኀጢ​አት ፈረ​ድ​ህ​ባ​ቸው። 24በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ዘንድ ያሉ የተ​ዋ​ረዱ ከብ​ቶ​ችን አማ​ል​ክት እያሉ ብዙ ዘመን በስ​ሕ​ተት ጐዳና ተጐ​ድ​ተ​ዋ​ልና፥ ዕው​ቀት እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ልጆ​ችም ሐሰ​ትን ተና​ገሩ። 25ስለ​ዚ​ህም ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ሕፃ​ናት ስለ​ሆኑ እንደ ዋዛ​ቸው መጠን ፍር​ድን በእ​ነ​ርሱ ላይ አመ​ጣህ። 26በቍ​ጣው ተግ​ሣጽ ካል​ተ​መ​ለሱ የጻ​ድቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ር​ዱን እን​ጀራ ይቅ​መሱ፤ እነ​ርሱ ባገ​ኛ​ቸው መከራ አን​ጐ​ራ​ጕ​ረ​ዋ​ልና፥ ቸልም ብለ​ዋ​ልና። 27አማ​ል​ክት እንደ ሆኑ ባሰ​ቧ​ቸው በእ​ነ​ዚህ በጣ​ዖ​ታቱ በተ​ፈ​ረ​ደ​ባ​ቸው ጊዜ ቀድሞ የካ​ዱ​ትን ያው​ቁ​ታል፥ ጻድቅ አም​ላክ እንደ ሆነም ያው​ቁ​ታል፤ ስለ​ዚ​ህም ፍጹም የፍ​ርድ ቅጣት ደረ​ሰ​ባ​ቸው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ