መጽሐፈ ጥበብ 10
10
ጥበብ ሰውን እንደምትጠብቅ
1ይህቺ አስቀድሞ የተፈጠረ የዓለምን አባት ጠበቀች፥ ብቻውንም ከተፈጠረ በኋላ እንደ አደራ ጠበቀችው፥ ከራሱ በደልም አዳነችው። 2ሁሉንም ይገዛና ይይዝ ዘንድ ኀይልን ሰጠችው ። 3በደለኛና ግፈኛ ሰውም በቍጣው ከእርሷ በራቀ ጊዜ፥ ወንድሞቻቸውን ከሚገድሉ ሰዎች ጋር በመዓት ጠፋ። 4ዳግመኛም ምድር በማየ አይኅ በጠፋች ጊዜ ጥበብ ጻድቁን አዳነችው፥ በተናቀ እንጨት ዕቃም አሻገረችው። 5አሕዛብ ወደ ተለያየ ክፋትና ጥመት ተጨልጠው በሄዱ ጊዜ ጻድቁን አመለከተችው፤ ያለ በደልና ያለ ነውር ለእግዚአብሔር ጠበቀችው፤ በቸርነትም የጸና ልጁን ጠበቀች።
6ይህቺ ከሚጠፉ ዝንጉዎች ሰዎች ለይታ ጻድቁን ልጅ አዳነች፥ በአምስቱ ከተሞችም ላይ እሳት በወረደች ጊዜ በመሸሽ አዳነችው። 7ለክፋታቸው ምስክር ልትሆን እስከ ዛሬ ድረስ ምድረ በዳ ሆና እየጤሰች አለች፥ ተክሎችዋም በጊዜዋ ቢያፈሩ ፍጹማን ያልሆኑ ናቸው፤ ያላመነች ሰውነትም መታሰቢያ ሆኖ የሚታይ የጨው ድንጋይ ሆና ቆማለች።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ላላመነች ሰውነትም መታሰቢያ ትሆን ዘንድ የጨው ሐውልት ቆማለች” ይላል። 8እነዚህ ጥበብን የተላለፉ ናቸውና ደግ ነገርን ባለማወቅ የደረሰባቸውን መዓት በማወቅ እንደ እነዚያ የጠፉ ብቻ አይደለም። ነገር ግን የበደሉትን በደል መሰወር እንዳልተቻላቸው መጠን ለስንፍናቸው መታሰቢያን በዚህ ዓለም ተዉ። 9ጥበብስ የሚያገለግሏትን ሰዎች ከድካምና ከመከራ አዳነች።
10ይህች ከወንድሙ ቍጣ የተነሣ የሸሸውን ጻድቅ ሰው ወደ ቀና መንገድ መራችው። የእግዚአብሔርንም መንግሥት አሳየችው፤ የተቀደሱትንም ማወቅን ሰጠችው፥ ከድካሙ የተነሣም አበለጸገችው፥ ጥሪቱንም አበዛችለት። 11ከሚቀሙትና ከሚበረታቱበትም ሰዎች የተነሣ ጠበቃ ሆና ቆመችለት፤ ረዳችውም። 12ከጠላቶቹም እንደ አደራ ዕቃ ጠበቀችው፥ ከከበቡትም ሰዎች አዳነችው። ለእግዚአብሔርም በበጎ መገዛት ከሁሉ እንደሚጸና ያውቅ ዘንድ በጽኑ ገድል ጊዜ ድልን ሰጠችው።
13ይሀቺ ጥበብ በተሸጠ ጊዜ ጻድቁን ሰው አልተለየችውም፤ ነገር ግን ወደ ጕድጓድ ከእርሱ ጋር ወረደች፥ ከኀጢአትም አዳነችው። 14በተበረታቱበትም ሰዎች ላይ ግዛትንና የመንግሥትን ሹመት እስከምታመጣለት ድረስ በታሠረበት አልተለየችውም። የናቁትንና ያነወሩትንም ሐሰታቸውን ገለጠችባቸው። የዘለዓለምንም ክብር ሰጠችው።
ጥበብ እስራኤልን ከግብፅ መርታ እንዳወጣቻቸው
15ይህቺም ጥበብ ጻድቅ ሕዝብን፥ ነቀፋ የሌለበት ዘርንም ከሚያስጨንቋቸው አሕዛብ አዳነች። 16በእግዚአብሔር ባሪያ ሰውነትም አደረች፤ በተአምራትና በድንቅ ሥራዎችም የሚያስደነግጡ ነገሥታትን ተቃወመች። 17ለቅዱሳንም የድካማቸውን ዋጋ ሰጠቻቸው፥ የተደነቀ መንገድንም መራቻቸው፥ በቀንም ጥላ ሆነቻቸው፥ በሌሊትም ስለ ከዋክብት ብርሃን ፈንታ ብርሃን ሆና አበራችላቸው። 18የሚያስፈራ የኤርትራ ባሕርንም አሻገረቻቸው፥ በብዙ ውኃ መካከልም አሳለፈቻቸው። 19ጠላቶቻቸውን ግን አሰጠመች፥ እነርሱንም ከጥልቅ ባሕር አወጣቻቸው። 20ስለዚህም ነገር ጻድቃን ክፉዎችን ማረኩ። አቤቱ ቅዱስ ስምህንም አመሰገኑ። ተዋጊና አሸናፊ እጅህንም በአንድነት አከበሩ። 21ጥበብ የዲዳዎችን አፍ ከፍታለችና፥ የሕፃናትንም አንደበት ቀንቶ የሚናገር አድርጋለችና።
Currently Selected:
መጽሐፈ ጥበብ 10: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ