መጽሐፈ ሲራክ 42
42
1ነገር ግን ስለዚህ ነገር አትፈር፤
ስለ እግዚአብሔርም ሕግ በደል እንዳይሆንብህ የሰው ፊት አይተህ አታዳላ፤
2ስለ ልዑል ሕግና ስለ ቃል ኪዳኑ አትፈር፤
በደለኛውንም እንዳታነጻው ስለ ፍርድ አትፈር።
3ከጓደኛህ ጋር ገንዘብህን በተሳሰብህ ጊዜ አትፈር፤
ስለ ዋጋህና ስለ ርስትህ አትፈር።
4ስለ ሚዛንና ስለ ላዳንም ጥቂት ቢሆን፥ ብዙም ቢሆን
ስለ ገንዘብህ አትፈር።
5ስለሚረባህና ስለሚጠቅምህም ሁሉ አትፈር፤#ግሪኩ “በንግድ ስለሚገኘውም ትርፍ አትፈር” ይላል።
ልጆችህንም ስለ ማስተማር አትፈር፤
ክፉ ባሪያንም ጎን ጎኑን ግረፈው።
6በክፉ ሴት ላይ ቍልፍ መያዝ መልካም ነው፤
ብዙ እጆች ካሉበት ዘንድም በቍልፍ አኑር።
7የምትሠራውን ሁሉ በቍጥር፥ በመስፈሪያና በሚዛን አድርግ፤
ያገባኸውና ያወጣኸው፥#“ያገባኸውንና ያወጣኸውን” የሚለው በግሪኩ የለም። የሰጠኸውና የተቀበልኸው ሁሉ በጽሑፍ ይሁንህ።
8ሰነፍን ሰው፥ አእምሮ የሌለውንም ሰው፥
በእርጅናውም ወደ ዝሙት የሚሄድ ሽማግሌን ስለ መምከር አትፈር፤
ስለዚህ በሰው ሁሉ ዘንድ በእውነት ብልህና ዐዋቂ ትሆናለህ።
9ሴት ልጅ ለአባትዋ ስውር የእንቅልፍ ዕጦት ናት፤
የወጣትነት ዕድሜዋ እንዳያልፍባት፥ ከተዳረችም በኋላ እንዳትጠላ፥
ስለ እርስዋ ማሰብ ዕንቅልፍን ያሳጣዋል፤
10በድንግልናዋ እንዳትደፈር፥
በአባቷም ቤት ፀንሳ እንዳትገኝ፥
ምንአልባትም ከባልዋ ጋር ሳለች እንዳትበድል፥
ካገባችም በኋላ መካን እንዳትሆን፥
11የጠላት መዘባበቻ፥ በከተማም መነጋገሪያ፥
በሕዝቡም መካከል መሰደቢያ እንዳታደርግህ፥
በብዙ ሰዎች ፊትም እንዳታሳፍርህ የማታፍር ልጅን አጽንተህ ጠብቃት።
12ለሰው ሁሉ ስለ መልኩ አታድላለት፤
በሴቶችም መካከል አትግባ፤
13ከልብስ ብል ይገኛል፤
ክፋትም ሁሉ ከሴቶች ይገኛል።
14ኀፍረትንና ቅንዐትን ከምታመጣ ሴት ደግነት፤
የወንድ ክፋት ይሻላል።
የእግዚአብሔር ክብር በፍጥረቱ
15እንግዲህ ወዲህ ግን የእግዚአብሔርን ሥራ አስባለሁ፤
ያየሁትንም እናገራለሁ፤
ፍጥረት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥሯልና።
16ፀሐይ ያበራል፤ ሁሉንም ያሳያል፤
የእግዚአብሔርም ጌትነት በሥራው ሁሉ ላይ ምሉእ ነው።
17ሁሉ በክብሩ ይጸና ዘንድ፥
ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ያጸናውን አላደረገምን?#በግሪክ ሰባ. ሊ. በጥያቄ አይደለም።
18ጥልቅንና ልብን መርምሮ ያውቃቸዋል፤
ምክራቸውንም ሁሉ ያውቃል፤
እግዚአብሔር የልቡና አሳብን ሁሉ ያውቃል፤
የዓለምንም ምልክት ያያል።
19ያለፈውንም፥ የሚመጣውንም እርሱ ይናገራል፤
የተሰወረውንም ፍለጋ ይገልጣል።
20ከምክርም ሁሉ የሚያመልጠው የለም፤
ከነገሩ ሁሉ አንድ ቃል ስንኳ የሚሰወረው የለም።
21የጥበቡን ገናናነት አስጌጠ።
ይህቺም ዓለም ሳይፈጠር የነበረች ናት፥
ለዘለዓለሙም ትኖራለች፤ አትጨምርም፤ አትጐድልምም፤
አንድ መካርን ስንኳ አይፈልግም።
22ሥራው ሁሉ ያማረ ነው፤
ለማየትም እንደ ብርሃን ነው፤
23ይህ ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ይኖራል፤
ለጥቅም በሚፈልጉት ጊዜ ይሰማል።
24ሁሉም አንዱ የሌላው ተቃራኒ በመሆን ሁለት ሁለት ናቸው፤
ምንም ነጠላ አድርጎ የፈጠረው የለም።
25ለመልካም ነገር አንዱን ከሁለተኛው ጋር አጸናው፤
ክብሩን ከማየት ማን ይጠግባል?
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 42: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 42
42
1ነገር ግን ስለዚህ ነገር አትፈር፤
ስለ እግዚአብሔርም ሕግ በደል እንዳይሆንብህ የሰው ፊት አይተህ አታዳላ፤
2ስለ ልዑል ሕግና ስለ ቃል ኪዳኑ አትፈር፤
በደለኛውንም እንዳታነጻው ስለ ፍርድ አትፈር።
3ከጓደኛህ ጋር ገንዘብህን በተሳሰብህ ጊዜ አትፈር፤
ስለ ዋጋህና ስለ ርስትህ አትፈር።
4ስለ ሚዛንና ስለ ላዳንም ጥቂት ቢሆን፥ ብዙም ቢሆን
ስለ ገንዘብህ አትፈር።
5ስለሚረባህና ስለሚጠቅምህም ሁሉ አትፈር፤#ግሪኩ “በንግድ ስለሚገኘውም ትርፍ አትፈር” ይላል።
ልጆችህንም ስለ ማስተማር አትፈር፤
ክፉ ባሪያንም ጎን ጎኑን ግረፈው።
6በክፉ ሴት ላይ ቍልፍ መያዝ መልካም ነው፤
ብዙ እጆች ካሉበት ዘንድም በቍልፍ አኑር።
7የምትሠራውን ሁሉ በቍጥር፥ በመስፈሪያና በሚዛን አድርግ፤
ያገባኸውና ያወጣኸው፥#“ያገባኸውንና ያወጣኸውን” የሚለው በግሪኩ የለም። የሰጠኸውና የተቀበልኸው ሁሉ በጽሑፍ ይሁንህ።
8ሰነፍን ሰው፥ አእምሮ የሌለውንም ሰው፥
በእርጅናውም ወደ ዝሙት የሚሄድ ሽማግሌን ስለ መምከር አትፈር፤
ስለዚህ በሰው ሁሉ ዘንድ በእውነት ብልህና ዐዋቂ ትሆናለህ።
9ሴት ልጅ ለአባትዋ ስውር የእንቅልፍ ዕጦት ናት፤
የወጣትነት ዕድሜዋ እንዳያልፍባት፥ ከተዳረችም በኋላ እንዳትጠላ፥
ስለ እርስዋ ማሰብ ዕንቅልፍን ያሳጣዋል፤
10በድንግልናዋ እንዳትደፈር፥
በአባቷም ቤት ፀንሳ እንዳትገኝ፥
ምንአልባትም ከባልዋ ጋር ሳለች እንዳትበድል፥
ካገባችም በኋላ መካን እንዳትሆን፥
11የጠላት መዘባበቻ፥ በከተማም መነጋገሪያ፥
በሕዝቡም መካከል መሰደቢያ እንዳታደርግህ፥
በብዙ ሰዎች ፊትም እንዳታሳፍርህ የማታፍር ልጅን አጽንተህ ጠብቃት።
12ለሰው ሁሉ ስለ መልኩ አታድላለት፤
በሴቶችም መካከል አትግባ፤
13ከልብስ ብል ይገኛል፤
ክፋትም ሁሉ ከሴቶች ይገኛል።
14ኀፍረትንና ቅንዐትን ከምታመጣ ሴት ደግነት፤
የወንድ ክፋት ይሻላል።
የእግዚአብሔር ክብር በፍጥረቱ
15እንግዲህ ወዲህ ግን የእግዚአብሔርን ሥራ አስባለሁ፤
ያየሁትንም እናገራለሁ፤
ፍጥረት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥሯልና።
16ፀሐይ ያበራል፤ ሁሉንም ያሳያል፤
የእግዚአብሔርም ጌትነት በሥራው ሁሉ ላይ ምሉእ ነው።
17ሁሉ በክብሩ ይጸና ዘንድ፥
ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ያጸናውን አላደረገምን?#በግሪክ ሰባ. ሊ. በጥያቄ አይደለም።
18ጥልቅንና ልብን መርምሮ ያውቃቸዋል፤
ምክራቸውንም ሁሉ ያውቃል፤
እግዚአብሔር የልቡና አሳብን ሁሉ ያውቃል፤
የዓለምንም ምልክት ያያል።
19ያለፈውንም፥ የሚመጣውንም እርሱ ይናገራል፤
የተሰወረውንም ፍለጋ ይገልጣል።
20ከምክርም ሁሉ የሚያመልጠው የለም፤
ከነገሩ ሁሉ አንድ ቃል ስንኳ የሚሰወረው የለም።
21የጥበቡን ገናናነት አስጌጠ።
ይህቺም ዓለም ሳይፈጠር የነበረች ናት፥
ለዘለዓለሙም ትኖራለች፤ አትጨምርም፤ አትጐድልምም፤
አንድ መካርን ስንኳ አይፈልግም።
22ሥራው ሁሉ ያማረ ነው፤
ለማየትም እንደ ብርሃን ነው፤
23ይህ ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ይኖራል፤
ለጥቅም በሚፈልጉት ጊዜ ይሰማል።
24ሁሉም አንዱ የሌላው ተቃራኒ በመሆን ሁለት ሁለት ናቸው፤
ምንም ነጠላ አድርጎ የፈጠረው የለም።
25ለመልካም ነገር አንዱን ከሁለተኛው ጋር አጸናው፤
ክብሩን ከማየት ማን ይጠግባል?