መጽ​ሐፈ ሲራክ 38

38
ባለ መድ​ኀ​ኒ​ትና መድ​ኀ​ኒት
1ባለ መድ​ኀ​ኒ​ትን አክ​ብ​ረው፥
እንደ እጁ እን​ዲሁ ክብሩ ነውና።
እር​ሱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጥ​ሮ​ታ​ልና።
2ማዳን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ሲሆን፥
ክብ​ርን ግን ከን​ጉሥ ይቀ​በ​ላል።
3ሰው ሁሉ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ትን በጥ​በቡ ያከ​ብ​ረ​ዋል፤
በመ​ኳ​ን​ን​ትም ዘንድ ይመ​ሰ​ገ​ናል።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ትን ከም​ድር ፈጠረ፤
ጠቢብ ሰውም ይህን አይ​ን​ቀ​ውም።
5ኀይ​ሉን ያውቁ ዘንድ፥
ውኃ በእ​ን​ጨት የጣ​ፈጠ አይ​ደ​ለ​ምን?
6በጌ​ት​ነቱ ይከ​ብሩ ዘንድ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰ​ዎች ጥበ​ብን ሰጣ​ቸው።
7በመ​ድ​ኀ​ኒቱ ያድ​ና​ቸ​ዋል፤
በሽ​ታ​ቸ​ው​ንም ያር​ቅ​ላ​ቸ​ዋል።
8ያድኑ ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ መድ​ኀ​ኒ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤
እር​ሱም ለሀ​ገር ሰላ​ምን ያመ​ጣል።
9ልጄ ሆይ፥ በሽ​ታ​ህን ቸል አት​በል፤
ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸልይ፤
እር​ሱም ይፈ​ው​ስ​ሃል።
10ኀጢ​አ​ትን ተዋት፤ እጅ​ህን አቅና፤
ልቡ​ና​ህ​ንም ከኀ​ጢ​አት ሁሉ አንጻ።
11መባ​እ​ህን አግባ፤ የመ​ታ​ሰ​ቢ​ያ​ው​ንም የስ​ንዴ ዱቄት ስጥ፤
የሰባ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህ​ንም የተ​ቻ​ለ​ህን ያህል አብ​ዝ​ተህ አቅ​ርብ፤
12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን ፈጥ​ሮ​ታ​ልና፤
ለባለ መድ​ኀ​ኒት መን​ገ​ድን አብ​ጅ​ለት፥
እር​ሱ​ንም ትሻ​ዋ​ለ​ህና ከአ​ንተ አታ​ር​ቀው።
13በእ​ጃ​ቸው ፈውስ የሚ​ደ​ረ​ግ​በት ጊዜ አለና።
14ይረ​ዳ​ቸው ዘንድ፥ ዕረ​ፍ​ት​ንም ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥
ሁል​ጊ​ዜም ይፈ​ው​ሳ​ቸው ዘንድ እነ​ርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይለ​ም​ናሉ።
15ፈጣ​ሪ​ውን የሚ​በ​ድል በባለ መድ​ኀ​ኒት እጅ ይወ​ድ​ቃል።
ለሞተ ሰው መታ​ሰ​ቢያ ስለ ማድ​ረግ
16ልጄ ሆይ፥ ለሞተ ሰው አል​ቅ​ስ​ለት፥ እዘ​ን​ለ​ትም፤
ራስ​ህ​ንም አሳ​ዝን፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም መታ​ሰ​ቢያ አድ​ር​ግ​ለት።
ያገ​ለ​ገ​ለ​ህን ሰው ሞት ቸል አት​በል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ ሥር​ዐቱ ሰው​ነ​ቱን ገን​ዘው ፤ ቀብ​ሩ​ንም ችላ አት​በ​ለው” ይላል።
17እንደ ልማዱ መራራ ልቅሶ አል​ቅ​ስ​ለት፤
ጥልቅ ኀዘ​ንም እዘ​ን​ለት፥ የኀ​ዘን መዝ​ሙ​ርም ዘም​ር​ለት፤
እንደ ሕጉም አንድ ቀን ቢሆን ሁለት ቀን ቢሆን አል​ቅ​ስ​ለት።
18ከዚህ በኋላ ልቅ​ሶ​ህን ተው።
ኀዘ​ንም አይ​ግ​ባህ፤
በኀ​ዘን የሞቱ ብዙ​ዎች ናቸ​ውና፥
የልብ ኀዘ​ንም ኀይ​ልን ይሰ​ብ​ራ​ልና።
19ኀዘ​ንና ትካዜ ለሞት ያደ​ር​ሳል፤
የድ​ሃም ዘመኑ ሁሉ በኀ​ዘን ያል​ቃል።
20ኀዘ​ንን ወደ ልቡ​ናህ አታ​ግባ፤
ኀዘ​ንን ከአ​ንተ አር​ቃት።
21ድኅ​ነት እን​ደ​ሌ​ለ​ባት ዕወቅ፤ ራስ​ህ​ንም ትጎ​ዳ​ለህ፥
ታሳ​ዝ​ና​ለህ፥ የም​ት​ጠ​ቅ​መ​ውም ነገር የለም።
22እኔ የተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትን ፍዳ አስ​ተ​ውል፤
አን​ተም እን​ደ​ዚሁ ፍዳን እን​ደ​ም​ት​ቀ​በል ዕወቅ።
እኔ ዛሬ አን​ተም ነገ።
23የሞተ ሰውስ ዐረፈ፤
ነገር ግን መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውን አድ​ር​ግ​ለት፤
ከዚህ በኋላ ነፍሱ ታርፍ ዘንድ ልቅ​ሶ​ህን ተው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሞተ ሰው ባረፈ ጊዜ ተዝ​ካር ይሁ​ን​ለት ነፍ​ሱም ከእ​ርሱ በተ​ለ​የች ጊዜ ስለ እርሱ ተጽ​ናና” ይላል።
24የጸ​ሓፊ ጥበቡ በተ​ሾ​መ​በት ወራት ነው፤
ሥራ​ውን የማ​ያ​በዛ ሰው አይ​ራ​ቀ​ቅም።
25ዕር​ፉን የሚ​ያ​ጸና ሰው በም​ንም አይ​ራ​ቀ​ቅም፥
በእ​ር​ሻው ይታ​በ​ያል፥ በሬ​ው​ንም ይገ​ር​ፋል፤ በሥ​ራ​ውም ይመ​ላ​ለ​ሳል፤
ነገ​ሩም ሁሉ ስለ በሬና ወይ​ፈን ነው።
26አሳቡ እር​ሻ​ውን እን​ዲ​ያ​ርስ ነው፤
ትጋ​ቱም በሬ​ውን ገለባ ያበላ ዘንድ ነው፤
ወይ​ፈ​ኑ​ንም እስ​ኪ​ያ​ቀና ድረስ ይደ​ክ​ማል።
27ሌሊቱ ቀን የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ጠራ​ቢና የጠ​ራ​ቢ​ዎች አለቃ፥
የማ​ኅ​ተም ቅርጽ የሚ​ቀ​ር​ጹና የሚ​ያ​ለ​ዝቡ ሰዎች እንደ እርሱ ናቸው፤
እነ​ዚ​ህም አሳ​ባ​ቸው ሁሉ በየ​መ​ልኩ መስ​ለው ይሠሩ ዘንድ ነው፤
ምክ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ ማኅ​ተ​ሙን ማለ​ዘ​ብን ይጠ​ነ​ቀቁ ዘንድ ነው፤
ትጋ​ታ​ቸ​ውም ሥራ​ቸ​ውን ይፈ​ጽሙ ዘንድ ነው።
28በወ​ናፍ አጠ​ገብ የሚ​ቀ​መጥ፥ የብ​ረ​ት​ንም ሥራ የሚ​ማር አን​ጥ​ረኛ እንደ እርሱ ነው።
የወ​ና​ፉም ጢስ ሰው​ነ​ቱን ያሻ​ክ​ረ​ዋል።
እሳ​ቱም ሰው​ነ​ቱን ያቀ​ል​ጣ​ታል፤ የመ​ዶ​ሻ​ውም ድምፅ ጆሮ​ውን ያደ​ነ​ቍ​ረ​ዋል።
ዐይ​ኖ​ቹም ወደ መሣ​ሪ​ያው ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤
በል​ቡም ሥራ​ውን ይጨ​ርስ ዘንድ ያስ​ባል፤
ትጋ​ቱም መሣ​ሪ​ያ​ው​ንና ወና​ፉን ያሳ​ምር ዘንድ ነው።
29በሥ​ራው የሚ​ቀ​መጥ ሸክላ ሠሪም እንደ እርሱ ነው፥
በእ​ግ​ሩም መን​ኰ​ራ​ኵ​ርን ያዞ​ራል፤
ሥራ​ው​ንም እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ፈ​ጽም ሁል​ጊዜ ያስ​ባል።
የሠ​ራ​ው​ንም ሁሉ ይቈ​ጥ​ራል።
30በእ​ጁም ጭቃ​ውን መስሎ ይሠ​ራል፤
በእ​ግሩ ጭቃ​ውን ሲረ​ግጥ ኀይ​ሉን ያደ​ክ​ማል፤
የል​ቡ​ና​ውም አሳብ ሥራ​ውን ይጨ​ርስ ዘንድ ነው።
ትጋ​ቱም መወ​ል​ወ​ያ​ውን ያዞር ዘንድ ነው።
31እነ​ዚህ ሁሉ የእ​ጃ​ቸ​ውን ሥራ ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤
ሁሉም በሥ​ራ​ቸው ይራ​ቀ​ቃሉ።
32ያለ እነ​ር​ሱም ሀገር መኖር አት​ች​ልም።
33ነገር ግን በሸ​ንጎ ምክ​ርን አያ​ስ​መ​ክ​ሯ​ቸ​ውም፤
በአ​ደ​ባ​ባ​ይም ከመ​ኳ​ን​ንት ጋራ አያ​ስ​ቀ​ም​ጧ​ቸ​ውም፤
የቅ​ጣት ፍር​ድ​ንም አያ​ስ​ፈ​ር​ዷ​ቸ​ውም፤ አያ​ስ​ገ​ዟ​ቸ​ውም፤ አያ​ሠ​ለ​ጥ​ኗ​ቸ​ው​ምም።
34ነገ​ርን መስሎ በመ​ና​ገር አይ​ኖ​ሩም፤
ነገር ግን ያገ​ርን ፈቃድ ያጸ​ናሉ፤ ጸሎ​ታ​ቸ​ውም በሥ​ራ​ቸው ይራ​ቀቁ ዘንድ ነው።
35 # ምዕ. 38 ቍ. 35 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የምዕ. 39 ቍ. 1 ነው። ዕው​ቀት ግን በልቡ ለሚ​ተጋ ሰው ነው።
የል​ዑ​ል​ንም ሕግ ለሚ​ያ​ስብ ሰው ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ