መጽ​ሐፈ ሲራክ 37

37
1ወዳጅ ያበጀ ሰው ሁሉ እኔም ወዳጁ ነኝ ይላል፤
ነገር ግን በከ​ንቱ ለስም ወዳጅ የሚ​ሆን ሰው አለ።
2በል​ቡ​ናው ግን እስ​ከ​ሚ​ሞ​ት​በት ቀን ድረስ ኀዘን ይኖ​ራል፤
ጠላት የሚ​ሆን ወዳ​ጅም አለ።
3ክፉ ምኞት ሆይ! ከወ​ዴት ተገ​ኘሽ፤
በም​ድሩ ሁሉ ኀጢ​አ​ትን መላሽ።
4በደ​ስ​ታህ ጊዜ የሚ​ቀ​ር​ብህ ወዳጅ አለ፤
ብት​ቸ​ገር ግን እርሱ ጠላት ይሆ​ን​ሃል።
5በበ​ሽ​ታህ ጊዜ ስለ ሆዱ የሚ​ያ​ዝ​ን​ልህ ወዳጅ አለ፤
የሚ​ከ​ዳህ ሰው ቢኖር ግን ይገ​ድ​ልህ ዘንድ እርሱ ይቀ​ድ​ማል።
6በተ​መ​ቸህ ጊዜ ወዳ​ጅ​ህን አት​ርሳ፤
ገን​ዘ​ብም ብታ​ገኝ አት​ተ​ወው።
7መካር ሁሉ ምክ​ርን ይመ​ክ​ራል፤
ነገር ግን ራሱን ይጠ​ቅም ዘንድ የሚ​መ​ክር ሰው አለ።
8ከሚ​መ​ክ​ርህ ሰው ልቡ​ና​ህን ጠብቅ፤
ስለ ራሱ ይመ​ክ​ር​ሃ​ልና፤ ይወ​ድ​ድ​ህም ዘንድ አስ​ቀ​ድ​መህ ፍላ​ጎ​ቱን ዕወ​ቅ​በት።
9ገን​ዘ​ብ​ህን የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ብ​ህን ነገር ያመ​ጣ​ብ​ሃል#ግሪክ ሰባ. ሊ. ልዩ​ነት ያሳ​ያል።
በጎ ነገር አደ​ረ​ግህ ይል​ሃል፤
በተ​ቸ​ገ​ር​ህም ጊዜ አይቶ ይስ​ቅ​ብ​ሃል።
10ከሚ​ጠ​ባ​በ​ቅህ ሰው ጋራ አት​ማ​ከር፤
ከሚ​መ​ቀ​ኝ​ህም ሰው ነገ​ር​ህን ሰውር።
11ከሴት ጋር ስለ​ሚ​ያ​ስ​ቀ​ናት ነገር አት​ና​ገር፤
ስለ ጦር​ነ​ትም ከፈሪ ሰው ጋር አት​ማ​ከር።
ስለ ትር​ፍም ከሻጭ ጋር አት​ማ​ከር፤
ስለ ንግድ ነገ​ርም ከነ​ጋዴ ጋር አት​ማ​ከር።
ስለ ምጽ​ዋ​ትም ከን​ፉግ ሰው ጋር አት​ማ​ከር።
ዋጋን ስለ መመ​ለ​ስም ከከ​ዳ​ተኛ ጋር አት​ማ​ከር፤
ስለ ሥራም ከሰ​ነፍ ሰው ጋራ አት​ማ​ከር፤
ሥራ ስለ​ሚ​ፈ​ጸ​ም​በት ዓመ​ትም ከም​ን​ደኛ ጋር አት​ማ​ከር።
ስለ ጥበ​ብም ከአ​ላ​ዋቂ ሰው ጋር አት​ማ​ከር፤
ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ስለ​ዚህ ነገር የም​ት​ማ​ከ​ረው አይ​ኑር።
12ሃይ​ማ​ኖት እን​ዳ​ለው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕግ​ጋ​ትን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ” ይላል። ከም​ታ​ው​ቀው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ከሚ​ፈራ፥
ልቡ​ና​ውም እንደ ልብህ ከሆነ ጻድቅ ሰው ጋር ምክ​ር​ህን ተና​ገር፤
ብታ​ዝ​ንም ከአ​ንተ ጋር ያዝ​ናል።
13እር​ስዋ ከሁሉ ይልቅ ታማ​ኝህ ናትና፤
የል​ቡ​ና​ህን ምክር አጽና።
14የሰው ልቡና ከሰ​ባት ጠባ​ቂ​ዎች ይልቅ
የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ትን ነገር ፈጽማ ታስ​ታ​ው​ቀ​ዋ​ለ​ችና።
15ከዚህ ሁሉ ጋር መን​ገ​ድ​ህን በእ​ው​ነት ያቀ​ና​ልህ ዘንድ፥
ወደ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለምን።
16የመ​ፍ​ቅድ ሁሉ መጀ​መ​ሪያ ቃል ነው፤
የሥ​ራም ሁሉ መጀ​መ​ሪያ ምክር ነው።
17የሰው የልቡ ምል​ክት በአ​ራቱ ወገን ይታ​ያል።
18እነ​ዚ​ህም ኀዘ​ንና ደስታ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ደግ​ነ​ትና ክፋት” ይላል። ሞትና ሕይ​ወት ናቸው።
እነ​ዚ​ህ​ንም ሁሉ አን​ደ​በት ያመ​ጣ​ቸ​ዋል።
19ሁሉን የሚ​ማር፥ ብዙም የሚ​ያ​ውቅ ሰው አለ፤
ነገር ግን ሰው​ነ​ቱን መጥ​ቀም አይ​ች​ልም።
20በነ​ገር የሚ​ራ​ቀቅ፥ ነገር ግን ራሱን የሚ​ያ​ስ​ጠላ ሰው አለ።
እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ጥቅሙ ሁሉ ያል​ፈ​ዋል።
21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሞገ​ስን አይ​ሰ​ጠ​ው​ምና
ከጥ​በ​ቡም ሁሉ ወጥ​ት​ዋ​ልና።
22በራሱ የሚ​ራ​ቀቅ፥
በቃ​ሉም የዋህ የሚ​ሆን ሰው አለ።
23ብልህ ሰው ወገ​ኖ​ቹን ይመ​ክ​ራ​ቸ​ዋል፤
ለዘ​መ​ዶ​ቹም ጥበ​ብን ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የማ​ስ​ተ​ዋ​ልም ፍሬ በአ​ን​ደ​በቱ አለ” ይላል።
24ብልህ ሰው በበ​ረ​ከት ይጠ​ግ​ባል፤
ያዩ​ትም ሰዎች ሁሉ ብፁዕ ይሉ​ታል።
25የሰው ዘመኑ በቍ​ጥር ነው፤
የእ​ስ​ራ​ኤል ዘመን ግን የማ​ይ​ቈ​ጠር ነው።
26ለወ​ገ​ኖቹ ጥበ​በኛ የሆነ ሰው ዋጋ​ውን ያገ​ኛል፤
ስሙም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።
27ልጄ ሆይ፥ በሕ​ይ​ወት ሳለህ ሰው​ነ​ት​ህን ፈት​ናት፥
የሚ​ጎ​ዳ​ት​ንም ዐው​ቀህ አት​ስ​ጣት፤
28ሁሉ ለሰ​ው​ነት የሚ​ገ​ባት አይ​ደ​ለ​ምና፥
ሁሉም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛት አይ​ደ​ለ​ምና፤
29ለመ​ብል ሁሉ አት​ሰ​ስት፤
ላየ​ኸ​ውም እህል ሁሉ አት​ሳሳ።
30ብዙ መብ​ላት ደዌ ይሆ​ና​ልና፤
ስስ​ትም ጓታን ያበ​ዛ​ዋ​ልና።
31ስስት የገ​ደ​ላ​ቸው ሰዎች ብዙ ናቸው፥
መጥኖ የሚ​በላ ሰው ግን ሰው​ነቱ ጤነኛ ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ