መጽ​ሐፈ ሲራክ 36

36
1ይፈ​ት​ኑት ዘንድ ነው እንጂ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰውን መከራ አያ​ገ​ኘ​ውም፤
ከመ​ከ​ራ​ዪ​ቱም ይድ​ናል።
2ብልህ ሰው መጽ​ሐፍ መስ​ማ​ትን ይወ​ድ​ዳል፤
የሚ​ጠ​ራ​ጠ​ርና በመ​ጽ​ሐፉ የማ​ያ​ምን ሰው ግን በጥ​ቅል ነፋስ መካ​ከል እን​ደ​ም​ት​ን​ጓ​ለል መር​ከብ ይሆ​ናል።
3ብልህ ሰው አምኖ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይገ​ዛል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የታ​መነ ወዳጁ ይሆ​ናል፤ ደስም ያሰ​ኘ​ዋል።
4የም​ት​ና​ገ​ረ​ውን ነገ​ር​ህን አዘ​ጋ​ጅ​ተህ አድ​ምጥ፤
የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ምክር አጽ​ን​ተህ ተና​ገር።
5የሰ​ነፍ ሰው ልቡና እንደ ሰረ​ገላ መን​ኰ​ራ​ኵር ነው፤
የፈሪ ሰው ምክ​ርም እን​ደ​ም​ት​ሽ​ከ​ረ​ከር እን​ዝ​ርት ነው።
6ጮሌ ፈረስ እንደ በጎ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አሽ​ሟ​ጣጭ” ይላል። ወዳጅ ነው።
በሚ​ጋ​ል​በ​ውም ሁሉ በታች ያሽ​ካ​ካል።
7የዓ​መቱ ቀን ሁሉ በፀ​ሐይ ብር​ሃን ጸንቶ ሲኖር፥
አን​ዲቱ ቀን ካን​ዲቱ ቀን በምን ትበ​ል​ጣ​ለች?
8ቀኑ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ይለ​ያል፤
የበ​ዓ​ላ​ቱም ጊዜ በቍ​ጥሩ ይታ​ወ​ቃል።
9ከቀ​ኑም የቀ​ደ​ሰ​ውና ያከ​በ​ረው አለ።
ከእ​ነ​ር​ሱም በየ​ጊ​ዜ​ያ​ቸ​ውና በየ​ቍ​ጥ​ራ​ቸው ክረ​ም​ት​ንና መጸ​ውን፥ በጋ​ንም#“ክረ​ም​ት​ንና መጸ​ውን፥ በጋ​ንም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ለየ።
10እኛ ሁላ​ችን የአ​ዳም ልጆች ከመ​ሬት ተገ​ኘን፤
አዳ​ምም ከመ​ሬት ተፈ​ጠረ።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጥ​በቡ ብዛት ለያ​ቸው፤
በየ​መ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም አዘ​ጋ​ጃ​ቸው።
12ከእ​ነ​ር​ሱም የባ​ረ​ካ​ቸ​ውና ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ጋ​ቸው አሉ፤
ከእ​ነ​ር​ሱም የቀ​ደ​ሳ​ቸ​ውና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው አሉ።
ከእ​ነ​ር​ሱም የረ​ገ​ማ​ቸ​ውና ያጐ​ሳ​ቈ​ላ​ቸው አሉ፤
እንደ ሥራ​ቸ​ውም የወ​ነ​ጀ​ላ​ቸው አሉ።
13እኛ ሁላ​ችን በእ​ርሱ ዘንድ በሸ​ክላ ሠሪ እጅ እን​ዳለ ጭቃ፥ ነን፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ደስ እን​ደ​ሚ​ያ​ሰ​ኘው አድ​ርጎ ይሠ​ራው ዘንድ በሸ​ክላ ሠሪ እጅ እንደ ጭቃ ነን” ይላል።
ፍጥ​ረቱ ሁሉ በመ​ን​ገ​ዶቹ ይሄ​ዳል፤ ሰውም እን​ዲሁ በፈ​ጣ​ሪው እጅ ነው፤
ለሁ​ሉም እንደ ሥራው ይከ​ፍ​ለ​ዋል።
14የክ​ፋት ተቃ​ራ​ኒዋ በጎ​ነት ናት፤
የሞ​ትም ተቃ​ራ​ኒዋ ሕይ​ወት ናት፤
እን​ደ​ዚሁ የጻ​ድቅ ተቃ​ራ​ኒው ኃጥእ ነው።
15ከዚህ ሁሉ ጋር የል​ዑ​ልን ፍጥ​ረ​ቶች ተመ​ል​ከት፤
አንዱ የሌ​ላው ተቃ​ራኒ ሆኖ ሁለት ሁለት ናቸው።
16እኔ ግን ከሁሉ በኋላ ተነ​ሥቼ ይኽን ነገር አሰ​ብ​ሁት፥
ከጥ​ን​ቱም ጀምሬ መረ​መ​ር​ሁት።
17አቤቱ በስ​ምህ የተ​ጠሩ ወገ​ኖ​ች​ህን ይቅር በል፤
የበ​ኵር ልጄ ያል​ሃ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ይቅር በል።
18ቅድ​ስት ከተ​ማ​ህን፥
ማረ​ፊያ ቦታ​ህን ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ይቅር በል።
19ጽዮ​ን​ንም የቃ​ል​ህን በረ​ከት ሙላት፤
ክብ​ር​ህ​ንም በወ​ገ​ኖ​ችህ ላይ ሙላ።
20አስ​ቀ​ድሞ ለፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ሕግ​ህን ስጣ​ቸው፤
ለስ​ም​ህም ነቢ​ያ​ትን አስ​ነሣ።
21ነቢ​ያ​ት​ህን ያም​ኗ​ቸው ዘንድ ተስፋ ላደ​ረ​ጉህ ዋጋ​ቸ​ውን ስጣ​ቸው።
አቤቱ የባ​ሮ​ችህ የነ​ቢ​ያ​ትን ጸሎ​ታ​ቸ​ውን ስማ፤
22የአ​ሮ​ን​ንም በረ​ከት በሕ​ዝ​ብህ ላይ አሳ​ድር፤
በም​ድር የሚ​ኖሩ ሰዎች ሁሉ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ብቻ እንደ ሆንህ ይወቁ።
23እህል ሁሉ ይበ​ላል፤ ወደ ሆድም ይወ​ር​ዳል፤
ነገር ግን ከእ​ህል የሚ​ጣ​ፍጥ እህል አለ።
24የእ​ህ​ልን ጣዕም ሁሉ ጕሮሮ ይለ​የ​ዋል፥
እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ የጠ​ቢብ ሰው ልብ የሐ​ሰት ነገ​ርን ይለ​ያል።
25ክፉ ልቡና ኀዘ​ንን ያመ​ጣል፤
ብዙ መከራ የተ​ቀ​በለ ሰውም ትዕ​ግ​ሥ​ትን ይለ​ም​ደ​ዋል።
26ወንድ ሁሉ ሚስት ያገ​ባል፤
ነገር ግን ከሴት የም​ት​ሻል ሴት አለች።
27የሴት ውበቷ ፊትን ያበ​ራ​ዋል፤
ከሰው ፈቃድ ሁሉ እርሷ ትበ​ል​ጣ​ለች።
28የዋህ ብት​ሆን፥ ቃሏም ያማረ ቢሆን፤
ባሏ እንደ ሌሎች ሰዎች አይ​ደ​ለም።
29ረዳቱ፥ መደ​ገ​ፊያ ምሰ​ሶ​ውም ናትና፥
ልባም ሴትን ያገባ ሰው ደስ​ታ​ውን አገኘ።
30ቅጥር የሌ​ለው ቤት ገን​ዘቡ እን​ዲ​ሠ​ረቅ፥
እን​ደ​ዚ​ሁም ሚስት የሌ​ለ​ችው ሰው ተቸ​ግሮ ይኖ​ራል።
31ከከ​ተማ ወደ ከተማ የሚ​ዞር ሌባን የሚ​ዋ​ሰው ማን ነው?
ልጆች የሌ​ሉት፥ ንብ​ረ​ትም የሌ​ለ​ውና በመ​ሸ​በት የሚ​ያ​ድር ሰውም እን​ዲሁ ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ