መጽ​ሐፈ ሲራክ 35

35
1አለ​ቃም አድ​ር​ገው ቢሾ​ሙህ ራስ​ህን አታ​ኵራ፤
ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ሁን፤
ኀዘ​ና​ቸ​ው​ንም እዘን፤ ተቀ​ም​ጠ​ህም ፍረ​ድ​ላ​ቸው።
2ሥራ​ህን ጨር​ሰህ ዕረፍ፤
መል​እ​ክ​ት​ህን ጨር​ሰህ የክ​ብር ዘው​ድን ታገኝ ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ ጋራ ደስ ይበ​ልህ።
3ሽማ​ግሌ ሆይ፥ ተና​ገር፤ ይገ​ባ​ሃ​ልም፥
ለበጎ ነገ​ርም ቸል አት​በል፤
የጥ​በ​ብ​ህ​ንም ነገር ተና​ገር።#ግሪኩ “ሙዚ​ቃ​ንም አታ​ደ​ና​ቅፍ” የሚል ይጨ​ም​ራል።
4ለመ​ረ​መ​ረህ ሰው ሁሉ ቃል​ህን አት​ና​ገር፤
እን​ዳ​ገ​ኘ​ህም አት​ራ​ቀቅ።#ግሪኩ “ጨዋታ በበ​ዛ​በት ሁሉ ቃል​ህን አት​ና​ገር ፤ ጥበ​ብ​ህን ለመ​ግ​ለጽ ምቹ ጊዜ አይ​ደ​ለ​ምና” ይላል።
5በወ​ርቅ ጌጥ ክቡር ዕንቍ ደስ እን​ደ​ሚ​ያ​ሰኝ፥
ዘፈ​ንም ወይን በሚ​ጠጡ ሰዎች ዘንድ እን​ዲሁ ነው።
6በወ​ርቅ ዝር​ግፍ ላይ ዕንቍ እን​ደ​ሚ​ያ​ምር፤
ዘፈ​ንና መሰ​ንቆ በመ​ጠጥ ቤት እን​ዲሁ ያማረ ነው።
7ጎል​ማሳ! ከተ​ፈ​ቀ​ደ​ልህ ተና​ገር፤
ዳግ​መ​ኛም ቢጠ​ይ​ቁህ በጭ​ንቅ ተና​ገር።
8አንድ ጊዜ ተና​ግ​ረህ፥ ወዲ​ያ​ውኑ ነገ​ር​ህን ጨርስ፤
እያ​ወ​ቅ​ህም በአ​ን​ደ​በ​ትህ ዝም በል።#ግሪኩ “እን​ደ​ሚ​ያ​ው​ቅና ዝም እን​ደ​ሚል ሰውም ሁን” ይላል።
9በታ​ላ​ላ​ቆች መካ​ከል አት​ቀ​መጥ፤#ግሪኩ “በታ​ላ​ላ​ቆች ሰዎች መካ​ከል በሆ​ንህ ጊዜ ራስ​ህን ከእ​ነ​ርሱ ጋር እኩል አታ​ድ​ርግ” ይላል።
ሌላ ሰውም ሲና​ገር ነገ​ር​ህን አት​ና​ገር።
10መብ​ረቅ ከነ​ጐ​ድ​ጓድ በፊት እን​ደ​ሚ​ሮጥ፥ እን​ዲሁ የሚ​ያ​ፍር ሰው መከ​በሩ በፊቱ ነው።
11ወደ ቤትህ ገብ​ተህ#ግሪኩ “በጊ​ዜው ውጣ መጨ​ረ​ሻም አት​ሁን” ይላል። ሁሉን በጊ​ዜው መጥ​ነህ አድ​ርግ፤
በዚ​ያም ደስ ይበ​ልህ ተጫ​ወ​ትም።
12የሚ​ገ​ባ​ው​ንና የሚ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም ሁሉ አድ​ርግ፤
የት​ዕ​ቢ​ትን ነገር እን​ዳ​ት​ና​ገር ዕወቅ፤
በቃ​ል​ህም አት​በ​ድል።
13ከዚህ ሁሉ ጋራ ፈጣ​ሪ​ህን አመ​ስ​ግ​ነው፤
እር​ሱም ከበ​ረ​ከቱ ሁሉ ያጠ​ግ​ብ​ሃል።
ሕግን መተ​ር​ጐም
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ለሕጉ ይገ​ዛል፤
ወደ እር​ሱም ፈጥ​ነው የሚ​ሄዱ ሰዎች መፍ​ቅ​ዳ​ቸ​ውን ያገ​ኛሉ።
15ሕጉ​ንም የሚ​ፈ​ል​ገው ከእ​ርሱ ይጠ​ግ​ባል፤
በእ​ርሱ የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን ይወ​ድ​ቃል፤ ይበ​ድ​ላ​ልም።
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩት ሰዎች ፍር​ድን ያገ​ኛሉ፤
በእ​ኩለ ቀንም ተበ​ቅሎ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ያጠ​ፋ​ላ​ቸ​ዋል።
17ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ግን የሚ​መ​ክ​ሩ​ትን አይ​ሰ​ማም፤
ሁሉም እንደ እርሱ ይመ​ስ​ለ​ዋል።
18ብልህ ሰው ያለ ምክር የሚ​ሠ​ራው ሥራ የለም፤
የሚ​ሠ​ራ​ውም ሥራ የበጀ ይሆ​ን​ለ​ታል፤
ፍር​ሀ​ትን የማ​ያ​ስብ ትዕ​ቢ​ተኛ ጠላት ግን ያለ ምክር ይሠ​ራል።
19ልጄ ሆይ፥ አንተ ግን ያለ ምክር የም​ት​ሠ​ራው ሥራ አይ​ኑር፤
የሠ​ራ​ኸ​ው​ንም ሥራ አታ​ጥፋ።
20በጥ​ፋት ድን​ጋይ እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከል፥
መን​ገድ በሌ​ለ​በት በም​ድረ በዳ አት​ሂድ።
21ጠላ​ት​ህን በም​ድረ በዳ አት​መ​ነው።
22በፈ​ቃ​ድህ የማ​ይ​ሄድ ልጅ​ህን ስንኳ አት​መ​ነው።
23በሠ​ራ​ኸው ሥራ ሁሉ ሰው​ነ​ት​ህን ደስ አሰ​ኛት፥
በሁ​ሉም ትእ​ዛ​ዙን ጠብቅ።
24ሕጉን የሚ​ጠ​ብቅ ሰው የመ​ጽ​ሓ​ፉን ትእ​ዛዝ ይሰ​ማል፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ያ​ምን ሰው የሚ​ያ​ጣው ነገር የለም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ