መጽ​ሐፈ ሲራክ 34

34
1በጎ ልቡ​ና​ንና የሚ​ጣ​ፍጥ እህ​ልን አይ​ን​ቁ​ትም፤
ለባ​ለ​ጸ​ግ​ነት መት​ጋት ፈጽሞ ሰው​ነ​ትን ያከ​ሳል፥
ገን​ዘ​ብ​ንም ማሰብ እን​ቅ​ል​ፍን ያሳ​ጣል።
2የሚ​ጠ​ራ​ጠ​ሩ​ትን ማሰብ በእ​ን​ጉ​ልቻ እን​ቅ​ል​ፍን ያስ​ረ​ሳል፤
ከባድ ሕማ​ምም ያተ​ጋል፥ እን​ቅ​ል​ፍ​ንም ያሳ​ጣል።
3ባለ​ጸጋ ገን​ዘብ ያደ​ልብ ዘንድ ይዞ​ራል፤
ባረ​ፈም ጊዜ በጥ​ጋብ ደስ ይለ​ዋል።
4ድሃ ገን​ዘብ በማ​ጣት ይደ​ክ​ማል፤
ባረ​ፈም ጊዜ ወደ ልመና ይመ​ለ​ሳል።
5ገን​ዘ​ብን የሚ​ወድ ሰው አይ​ጸ​ድ​ቅም፤
ኀጢ​አ​ት​ንም የሚ​ወ​ዳት ሰው ይከ​ተ​ላ​ታል።
6ስለ ገን​ዘብ የወ​ደቁ ሰዎች ብዙ ናቸው፤
ሞታ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ቸው አዩ​ኣት።
7ገን​ዘብ ለሚ​ፈ​ል​ጓት የእ​ን​ቅ​ፋት ዕን​ጨት ናት፤
ሰነፍ ሰው ሁሉ በእ​ር​ስዋ ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላል።
8ከኀ​ጢ​አት ንጹሕ የሆነ፥
ልቡ​ና​ው​ንም ከገ​ን​ዘብ በኋላ ያላ​ስ​ከ​ተለ ባለ​ጸጋ ብፁዕ ነው።
9ለወ​ገ​ኖቹ መል​ካም ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ማን​ነው?
እንጃ! እር​ሱን እና​ደ​ን​ቀ​ዋ​ለን።
10በእ​ርሱ የተ​ፈ​ተነ፥ ያል​ሳ​ተም
እር​ሱም መመ​ኪያ የሆ​ነው ማን ነው?
ኀጢ​አት መሥ​ራት ሲቻ​ለው ኀጢ​አት የማ​ይ​ሠራ ማን ነው? እንጃ።
ክፉ መሥ​ራት ሲቻ​ለ​ውስ ክፉ የማ​ያ​ደ​ርግ ሰው ማን ነው?
11በረ​ከቱ ትጸ​ና​ለች፤ ምጽ​ዋ​ቱም በአ​ሕ​ዛብ ሀገር ትሰ​ማ​ለች።
የማ​ዕድ ሥር​ዐት
12በታ​ላቅ ማዕ​ድም ብት​ቀ​መጥ
ለመ​ብ​ላት ጉሮ​ሮ​ህን አት​ክ​ፈት፤
ምግ​ቡም ምን ያህል ነው ብለህ አታ​ጋን፤
13የሰው ዐይን ክፉ እንደ ሆነ አስብ፤
ከሰው ዐይን የሚ​ከፋ ምን አለ?
ስለ​ዚ​ህም ነገር ዐይን ታለ​ቅ​ሳ​ለች።
14ላየ​ኸው ሁሉ አት​ሳሳ፤
እጅ​ህን አት​ን​ከር፤
ወጭ​ቱን ወደ አንተ አት​ጎ​ትት፥
ድስ​ቱ​ንም አት​ጥ​ረግ።
15ባል​ን​ጀ​ራህ የጋ​በ​ዘ​ህን ዕወቅ፤
ያቀ​ረ​በ​ል​ህ​ንም ሁሉ ተረዳ።
16ያቀ​ረ​ቡ​ል​ህን እንደ ብልህ ሰው ሁነህ ብላ፤
ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እን​ዳ​ታ​ስ​ጸ​ይፍ ስታ​ላ​ምጥ ምላ​ስ​ህን አታ​ጩህ።
17እንደ ብልህ ሰው ሁሉ አስ​ቀ​ድ​መህ ተው፤ አት​ሳሳ፤
እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ግብ ሰውም አት​ሁን።
18በብ​ዙ​ዎች መካ​ከ​ልም ብት​ቀ​መጥ
እጅ​ህን አስ​ቀ​ድ​መህ አት​ስ​ደድ።
19በመ​ኝ​ታህ ሆድ​ህን እን​ዳ​ይ​ከ​ብ​ድህ፥
ጥቂት እን​ደ​ሚ​በ​ቃው እንደ ዐዋቂ ሰው መጥ​ነህ ብላ።
20መጥኖ የሚ​መ​ገብ ሰው እን​ቅ​ልፉ ጤና ነው፤
ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም በጧት በነቃ ጊዜ ሆዱን አይ​ከ​ብ​ደ​ውም፤
ለማ​ይ​ጠ​ግብ ለስሱ ሰው በሽ​ታው ቍን​ጣን፥ ጓታና ብስና ነው።
21ትበላ ዘንድ ግድ ቢሉህ ቀድ​መ​ሃ​ቸው ተነሥ፤
ከመ​ብ​ላ​ትም ዕረፍ።
22ልጄ ሆይ አድ​ም​ጠኝ፤ ምክ​ሬ​ንም አት​ናቅ፤
ኋላ ነገ​ሬን ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤
ምንም እን​ዳ​ታጣ በም​ት​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ደካማ አት​ሁን።
23ለጋ​ስን ሰው በሥ​ራው ማማር ይመ​ር​ቁ​ታል፤
የደ​ግ​ነቱ ምስ​ክ​ር​ነ​ትም የታ​መነ ነው፤
ንፉግ ሰው​ንም በክፉ ሥራው ይረ​ግ​ሙ​ታል።
የክ​ፋቱ ምስ​ክ​ር​ነ​ትም የተ​ረዳ ነው።
24መጠጥ ብዙ ሰዎ​ችን አስ​ት​ዋ​ቸ​ዋ​ልና፥
ወይን በጠ​ጣህ ጊዜ አት​ታ​በይ።
25ጽኑ ብረ​ትን በወ​ናፍ ይፈ​ት​ኑ​ታል፤
እን​ዲ​ሁም ሁሉ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ልቡና ወይን ይፈ​ት​ነ​ዋል።
26የሰው ሕይ​ወቱ ወይን መጠ​ጣት ነው፤
መጥኖ ለሚ​ጠ​ጣ​ውም ሰው ደስታ ነው፤
እርሱ ለሰው ደስታ ሊሆን ተፈ​ጥ​ሯ​ልና
ወይን ለማ​ይ​ጠጣ ሰው ሕይ​ወቱ ምን​ድን ነው?
27ለልብ ደስታ ነው፤ ለሰ​ው​ነ​ትም ሐሤት ነው፤
ወይ​ንን መጥኖ በጊ​ዜው መጠ​ጣት መል​ካም ነው።
28ወይን የል​ቡና ኀዘ​ንን ያስ​ረ​ሳል፤
ለሚ​ያ​ለ​ቅ​ስና ለሚ​ያ​ዝን ሰውም ወይ​ንን አጠ​ጣው።
29ሰነፍ ሰው ወይን በጠጣ ጊዜ ክር​ክ​ርን ያበ​ዛል፥ ይስ​ታል፥ ይበ​ድ​ላ​ልም፤
የመ​ጠጥ ብዛት ኀይ​ልን አያ​ስ​ገ​ኝም፤ ቍስ​ል​ንም አያ​ሳ​ጣም።
30ወይን ጠጥቶ ሳለ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን አት​ቈ​ጣው፤
ልቡ ደስ ብሎት ሳለም አታ​ሳ​ዝ​ነው፤
የም​ት​ነ​ቅ​ፈ​ው​ንም አት​ን​ገ​ረው፤
እርሱ ሰክሮ ሳለ ጉዳ​ይ​ህን አት​ለ​ም​ነው፤ አት​ዘ​ብ​ዝ​በ​ውም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ