መጽ​ሐፈ ሲራክ 31

31
ስለ ሕልም ከን​ቱ​ነት
1ሰነፍ ሰው ግን ሐሰ​ትን በከ​ንቱ ተስፋ ያደ​ር​ጋ​ታል፤
ሕል​ምም ሰነፍ ሰውን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ዋል።
2ሕል​ምን የሚ​ያ​ምን ሰው ጥላን እን​ደ​ሚ​ጨ​ብጥ፤
ነፋ​ስ​ንም እን​ደ​ሚ​ከ​ተል ነው።
3ሕልም ከዚህ ወደ​ዚህ ይሄ​ዳል፤
በየ​ም​ሳ​ሌ​ውም የእ​የ​ራ​ሱን ያሳ​ያል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕልም ለሌላ ነገር ያንድ ነገር እይታ ነው ፤ ለአ​ንድ ገጽም የሌላ መልክ ነው” ይላል።
4ከር​ኩስ ምን ንጹሕ ይወ​ጣል?
ከሐ​ሰ​ትስ እው​ነት ከየት ይገ​ኛል?
5ሕልም፥ ጥን​ቆ​ላና ሟርት ሁሉም ከንቱ ናቸው፤
ልብ​ንም ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ እንደ ምጥም ያጎ​ብ​ጣሉ።
6ይቅር ይል ዘንድ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ላከ ከአ​ል​ሆነ፥
በል​ብህ አታ​ኑ​ረው።
7ሕልም ብዙ ሰዎ​ችን አስ​ት​ዋ​ቸ​ዋ​ልና፤
እር​ሱ​ንም ተስፋ እያ​ደ​ረጉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና።
8ያለ ሐሰ​ትስ ከታየ በእ​ው​ነት ይደ​ር​ሳል፤
የእ​ው​ነት ቃልም የተ​ረዳ ይሆ​ናል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ልዩ​ነት አለው።
9የተ​ማረ ሰው ብዙ ምክ​ርን ያው​ቃል፤
ብዙ መከ​ራን የተ​ቀ​በለ ሰውም ጥበ​ብን ያስ​ተ​ም​ራል።
10ያል​ተ​ነካ ሰው ግን የሚ​ያ​ው​ቀው ነገር የለም።
11ብዙ መከራ የተ​ቀ​በለ ሰው ብዙ ትም​ህ​ርት ይማ​ራል።
12መከ​ራን በተ​ቀ​በ​ልሁ ጊዜ ብዙ አየሁ፤
ከአ​ሳ​ቤም ቃሌ በዛ።
13ለሞት እስ​ክ​ደ​ርስ ድረስ ሁል​ጊዜ መከ​ራን ተቀ​ብ​ያ​ለ​ሁና፤
ስለ​ዚ​ህም ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነ​ኛል።
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ ነፍስ ትድ​ና​ለች።
15እር​ሱን ተስፋ ያደ​ረጉ ሁሉ ይድ​ናሉ።
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰውን የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራው የለም፤
እርሱ አለ​ኝ​ታው ነውና አይ​ደ​ነ​ግ​ጥም።
17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ነፍስ ብፅ​ዕት ናት።
18እርሱ ያድ​ር​በ​ታ​ልና፥ የታ​መነ ወዳ​ጁም ነውና።
19የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖቹ ወደ ወዳ​ጆቹ ናቸው፤ ኀይሉ የታ​መነ ነው፤ ጥግ​ነ​ቱም ጽኑ ነው፤ ቃጠ​ሎ​ውን ያቀ​ዘ​ቅ​ዝ​ል​ሃል፤
ከቀ​ትር ፀሐ​ይም ይጋ​ር​ድ​ሃል፤
ከዕ​ን​ቅ​ፋት ይጠ​ብ​ቅ​ሃል፤ ከመ​ው​ደ​ቅም ይረ​ዳ​ሃል።
20ሰው​ነ​ት​ህን ያገ​ና​ታል፤ ዓይ​ኖ​ች​ህ​ንም ያበ​ራ​ቸ​ዋል፤
ይፈ​ው​ሳል፤ ደኅ​ን​ነ​ት​ንም ይሰ​ጣል፤ በረ​ከ​ት​ንም ያጠ​ግ​ባል።
21የበ​ደል መባእ መሥ​ዋ​ዕት ርኩስ ነው፤
የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም ቍር​ባ​ና​ቸው የረ​ከሰ ነው።
22የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም መባእ ተቀ​ባ​ይ​ነት የለ​ውም።
23በመ​ባህ ብዛት ኀጢ​አ​ትህ የሚ​ሰ​ረ​ይ​ልህ አይ​ደ​ለም።
24በዐ​መፃ ገን​ዘብ መባ​እን የሚ​ያ​ገባ ሰው፤
ሕፃ​ንን በአ​ባቱ ፊት እን​ደ​ሚ​ገ​ድል ሰው ነው።
25የድሃ ሕይ​ወቱ ምጽ​ዋት መለ​መን ነው፤
እምቢ ያለው ሰው ግን ነፍሰ ገዳይ ነው።
26ባልን ከሚ​ስቱ የሚ​ያ​ፋታ ሰው፥
ባል​ን​ጀ​ራ​ውን እን​ደ​ሚ​ገ​ድል ሰው ነው።
27የም​ን​ደ​ኛ​ውን ደመ​ወዝ የቀማ ሰው፥
ደሙን ማፍ​ሰሱ ነው።
28አንዱ ሲሠራ አንዱ ቢያ​ፈ​ርስ፥
የሁ​ለ​ቱስ ድካ​ማ​ቸው ምን ይጠ​ቅ​ማል?
29አንዱ ሲመ​ርቅ ሌላው ቢረ​ግም፥
ከሁ​ለቱ የማ​ና​ቸ​ውን ቃል ይሰ​ማል?
30ሬሳ ከዳ​ሰሰ በኋላ እጁን ቢታ​ጠብ፥
ዳግ​መኛ ሬሳ​ውን ከዳ​ሰሰ መታ​ጠቡ ምን ይጠ​ቅ​መ​ዋል?
31እን​ዲሁ ስለ ኀጢ​አቱ የሚ​ጾም ሰው ዳግ​መኛ ይበ​ድል ዘንድ ከሄደ፥
ከዚህ በኋላ ጸሎ​ቱን ማን ይሰ​ማ​ዋል?
ሰው​ነ​ቱ​ንስ ማሳ​ዘኑ ምን ይጠ​ቅ​መ​ዋል?

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ