መጽሐፈ ሲራክ 31
31
ስለ ሕልም ከንቱነት
1ሰነፍ ሰው ግን ሐሰትን በከንቱ ተስፋ ያደርጋታል፤
ሕልምም ሰነፍ ሰውን ያስደነግጠዋል።
2ሕልምን የሚያምን ሰው ጥላን እንደሚጨብጥ፤
ነፋስንም እንደሚከተል ነው።
3ሕልም ከዚህ ወደዚህ ይሄዳል፤
በየምሳሌውም የእየራሱን ያሳያል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕልም ለሌላ ነገር ያንድ ነገር እይታ ነው ፤ ለአንድ ገጽም የሌላ መልክ ነው” ይላል።
4ከርኩስ ምን ንጹሕ ይወጣል?
ከሐሰትስ እውነት ከየት ይገኛል?
5ሕልም፥ ጥንቆላና ሟርት ሁሉም ከንቱ ናቸው፤
ልብንም ያስደነግጣሉ፤ እንደ ምጥም ያጎብጣሉ።
6ይቅር ይል ዘንድ ከእግዚአብሔር የተላከ ከአልሆነ፥
በልብህ አታኑረው።
7ሕልም ብዙ ሰዎችን አስትዋቸዋልና፤
እርሱንም ተስፋ እያደረጉ ጠፍተዋልና።
8ያለ ሐሰትስ ከታየ በእውነት ይደርሳል፤
የእውነት ቃልም የተረዳ ይሆናል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ልዩነት አለው።
9የተማረ ሰው ብዙ ምክርን ያውቃል፤
ብዙ መከራን የተቀበለ ሰውም ጥበብን ያስተምራል።
10ያልተነካ ሰው ግን የሚያውቀው ነገር የለም።
11ብዙ መከራ የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርት ይማራል።
12መከራን በተቀበልሁ ጊዜ ብዙ አየሁ፤
ከአሳቤም ቃሌ በዛ።
13ለሞት እስክደርስ ድረስ ሁልጊዜ መከራን ተቀብያለሁና፤
ስለዚህም ነገር እግዚአብሔር ያድነኛል።
14እግዚአብሔርን የምትፈራ ነፍስ ትድናለች።
15እርሱን ተስፋ ያደረጉ ሁሉ ይድናሉ።
16እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውን የሚያስፈራው የለም፤
እርሱ አለኝታው ነውና አይደነግጥም።
17እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነፍስ ብፅዕት ናት።
18እርሱ ያድርበታልና፥ የታመነ ወዳጁም ነውና።
19የእግዚአብሔር ዐይኖቹ ወደ ወዳጆቹ ናቸው፤ ኀይሉ የታመነ ነው፤ ጥግነቱም ጽኑ ነው፤ ቃጠሎውን ያቀዘቅዝልሃል፤
ከቀትር ፀሐይም ይጋርድሃል፤
ከዕንቅፋት ይጠብቅሃል፤ ከመውደቅም ይረዳሃል።
20ሰውነትህን ያገናታል፤ ዓይኖችህንም ያበራቸዋል፤
ይፈውሳል፤ ደኅንነትንም ይሰጣል፤ በረከትንም ያጠግባል።
21የበደል መባእ መሥዋዕት ርኩስ ነው፤
የኀጢአተኞችም ቍርባናቸው የረከሰ ነው።
22የኀጢአተኞችም መባእ ተቀባይነት የለውም።
23በመባህ ብዛት ኀጢአትህ የሚሰረይልህ አይደለም።
24በዐመፃ ገንዘብ መባእን የሚያገባ ሰው፤
ሕፃንን በአባቱ ፊት እንደሚገድል ሰው ነው።
25የድሃ ሕይወቱ ምጽዋት መለመን ነው፤
እምቢ ያለው ሰው ግን ነፍሰ ገዳይ ነው።
26ባልን ከሚስቱ የሚያፋታ ሰው፥
ባልንጀራውን እንደሚገድል ሰው ነው።
27የምንደኛውን ደመወዝ የቀማ ሰው፥
ደሙን ማፍሰሱ ነው።
28አንዱ ሲሠራ አንዱ ቢያፈርስ፥
የሁለቱስ ድካማቸው ምን ይጠቅማል?
29አንዱ ሲመርቅ ሌላው ቢረግም፥
ከሁለቱ የማናቸውን ቃል ይሰማል?
30ሬሳ ከዳሰሰ በኋላ እጁን ቢታጠብ፥
ዳግመኛ ሬሳውን ከዳሰሰ መታጠቡ ምን ይጠቅመዋል?
31እንዲሁ ስለ ኀጢአቱ የሚጾም ሰው ዳግመኛ ይበድል ዘንድ ከሄደ፥
ከዚህ በኋላ ጸሎቱን ማን ይሰማዋል?
ሰውነቱንስ ማሳዘኑ ምን ይጠቅመዋል?
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 31: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 31
31
ስለ ሕልም ከንቱነት
1ሰነፍ ሰው ግን ሐሰትን በከንቱ ተስፋ ያደርጋታል፤
ሕልምም ሰነፍ ሰውን ያስደነግጠዋል።
2ሕልምን የሚያምን ሰው ጥላን እንደሚጨብጥ፤
ነፋስንም እንደሚከተል ነው።
3ሕልም ከዚህ ወደዚህ ይሄዳል፤
በየምሳሌውም የእየራሱን ያሳያል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕልም ለሌላ ነገር ያንድ ነገር እይታ ነው ፤ ለአንድ ገጽም የሌላ መልክ ነው” ይላል።
4ከርኩስ ምን ንጹሕ ይወጣል?
ከሐሰትስ እውነት ከየት ይገኛል?
5ሕልም፥ ጥንቆላና ሟርት ሁሉም ከንቱ ናቸው፤
ልብንም ያስደነግጣሉ፤ እንደ ምጥም ያጎብጣሉ።
6ይቅር ይል ዘንድ ከእግዚአብሔር የተላከ ከአልሆነ፥
በልብህ አታኑረው።
7ሕልም ብዙ ሰዎችን አስትዋቸዋልና፤
እርሱንም ተስፋ እያደረጉ ጠፍተዋልና።
8ያለ ሐሰትስ ከታየ በእውነት ይደርሳል፤
የእውነት ቃልም የተረዳ ይሆናል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ልዩነት አለው።
9የተማረ ሰው ብዙ ምክርን ያውቃል፤
ብዙ መከራን የተቀበለ ሰውም ጥበብን ያስተምራል።
10ያልተነካ ሰው ግን የሚያውቀው ነገር የለም።
11ብዙ መከራ የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርት ይማራል።
12መከራን በተቀበልሁ ጊዜ ብዙ አየሁ፤
ከአሳቤም ቃሌ በዛ።
13ለሞት እስክደርስ ድረስ ሁልጊዜ መከራን ተቀብያለሁና፤
ስለዚህም ነገር እግዚአብሔር ያድነኛል።
14እግዚአብሔርን የምትፈራ ነፍስ ትድናለች።
15እርሱን ተስፋ ያደረጉ ሁሉ ይድናሉ።
16እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውን የሚያስፈራው የለም፤
እርሱ አለኝታው ነውና አይደነግጥም።
17እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነፍስ ብፅዕት ናት።
18እርሱ ያድርበታልና፥ የታመነ ወዳጁም ነውና።
19የእግዚአብሔር ዐይኖቹ ወደ ወዳጆቹ ናቸው፤ ኀይሉ የታመነ ነው፤ ጥግነቱም ጽኑ ነው፤ ቃጠሎውን ያቀዘቅዝልሃል፤
ከቀትር ፀሐይም ይጋርድሃል፤
ከዕንቅፋት ይጠብቅሃል፤ ከመውደቅም ይረዳሃል።
20ሰውነትህን ያገናታል፤ ዓይኖችህንም ያበራቸዋል፤
ይፈውሳል፤ ደኅንነትንም ይሰጣል፤ በረከትንም ያጠግባል።
21የበደል መባእ መሥዋዕት ርኩስ ነው፤
የኀጢአተኞችም ቍርባናቸው የረከሰ ነው።
22የኀጢአተኞችም መባእ ተቀባይነት የለውም።
23በመባህ ብዛት ኀጢአትህ የሚሰረይልህ አይደለም።
24በዐመፃ ገንዘብ መባእን የሚያገባ ሰው፤
ሕፃንን በአባቱ ፊት እንደሚገድል ሰው ነው።
25የድሃ ሕይወቱ ምጽዋት መለመን ነው፤
እምቢ ያለው ሰው ግን ነፍሰ ገዳይ ነው።
26ባልን ከሚስቱ የሚያፋታ ሰው፥
ባልንጀራውን እንደሚገድል ሰው ነው።
27የምንደኛውን ደመወዝ የቀማ ሰው፥
ደሙን ማፍሰሱ ነው።
28አንዱ ሲሠራ አንዱ ቢያፈርስ፥
የሁለቱስ ድካማቸው ምን ይጠቅማል?
29አንዱ ሲመርቅ ሌላው ቢረግም፥
ከሁለቱ የማናቸውን ቃል ይሰማል?
30ሬሳ ከዳሰሰ በኋላ እጁን ቢታጠብ፥
ዳግመኛ ሬሳውን ከዳሰሰ መታጠቡ ምን ይጠቅመዋል?
31እንዲሁ ስለ ኀጢአቱ የሚጾም ሰው ዳግመኛ ይበድል ዘንድ ከሄደ፥
ከዚህ በኋላ ጸሎቱን ማን ይሰማዋል?
ሰውነቱንስ ማሳዘኑ ምን ይጠቅመዋል?