መጽሐፈ ሲራክ 30
30
ስለ ልጆች
1ልጁን የሚወድ ሰው በፍጻሜው በእርሱ ደስ ይለው ዘንድ፥
ልጁን መቅጣትን ቸል አይልም።
2ልጁን የሚቀጣ ሰው በእርሱ ደስ ይለዋል፤
በወዳጆቹም ዘንድ ይመካበታል።
3ልጁን ያስተማረ ሰው ጠላቱን ያስቀናል፥
በወዳጆቹም ዘንድ በእርሱ ደስ ይለዋል።
4ከእርሱ በኋላ እንደ እርሱ ያለ ልጅ ተክትዋልና
አባቱ ቢሞትም እንዳልሞተ ይሆናል።
5በሕይወቱም ሳለ በልጁ ደስ ይለዋል፤
ቢሞትም ልቡ አያዝንም።
6ከእርሱ በኋላ ጠላቶቹን የሚበቀል፥
ለወዳጆቹም ዋጋን የሚከፍል ልጅ ተክትዋልና።
7ልጆቹን የሚያባልግ ሰውነቱ ይቈስላል፤
በጩኸታቸውም ጊዜ ልቡ በሕመም ይሠቃያል።
8ያልተገራ ፈረስ ገርጋሪ ይሆናል፤
ያልተቀጣ ልጅም አውታታ ይሆናል፤
9ልጅህን ካቀማጠልኸው ይበረታታብህ ዘንድ ይመለሳል፤
ከእርሱም ጋር ብትጫወት ያሳዝንህ ዘንድ ይመለሳል።
10እንዳያሳዝንህም አትሳቅለት፤
በፍጻሜም ጥርስህን ያረግፍሃል።
11በወጣትነቱ ጊዜ ልጅህን ስድ አትልቀቀው።
በስሕተቱም ጊዜ ቸል አትበለው፤
12በአደገ ጊዜ እንዳያምፅብህ
በልጅነቱ ጊዜ ጎኑን ግረፈው።
13በእርሱ ጥፋት እንዳታፍር
ልጅህን ቅጣው፤ ያገለግልሃልም።
ስለ ጤንነት
14ሰውነቱ ከታመመና ሆዱ ከታሰረ ባለጸጋ፥
ሰውነቱ ጤነኛ የሆነና ሆዱ የተከፈተ ድሃ ይሻላል።
15ሰውነትህ ጤነኛ ይሁን፤
ሆድህም የተከፈተ ይሁን፤
ይህም ከባለጸግነት ሁሉ ይሻላል።
ከባለጸግነትና ከገንዘብም ሁሉ የሰውነት ጤንነት ይሻላል።
16በጤና ከመኖር ባለጸግነት አይመረጥም፤
ከልብ ደስታም የሚሻል ደስታ የለም።
17ከመረረ ኑሮና ከቍርጥማት በሽታ ሞት ይሻላል።
18በተዘጋ አፍ የሚቀርብ መብል
ወደ መቃብር እንደሚወሰድ እህል ነው።
19ለጣዖታት መሠዋት ምን ይጠቅማል?
እነርሱ አይበሉምና፥ እነርሱም አይጠጡምና፥
እነርሱም አያሸትቱምና፥
እግዚአብሔር የቀሠፈውም ሰው እንደዚሁ ነው።
20ጃንደረባ ቆንጆዪቱን ባቀፋት ጊዜ እንደሚያዝን፥
በዐይኖቹ እያየ ያዝናል።
21ነፍስህን አታሳዝን፤
ልብህንም አታስጨንቅ።
22የልቡና ደስታ ለሰው ሕይወቱ ነው፤
የሰውነት ደስታም ዘመንን ያረዝማል።
23ኀዘንን ከአንተ ታርቃት ዘንድ ልብህን አጽናናት፤
ሰውነትህንም አረጋጋት፤
ኀዘን ብዙ ሰዎችን አጥፍታቸዋለችና፤ ኀዘንም የምትጠቅመው የለምና።
24ቅናትና ቍጣ የሕይወት ዘመንን ያሳንሳሉ፤
ኀዘንም ጊዜው ሳይደርስ ያስረጃል።
25አጫጅን እየተከተለ እንደሚቃርም ሰው፤
በእግዚአብሔር በረከት ደረስሁ።
እንደ ወይን ለቃሚም መጭመቂያዬን ሞላሁ።
26ጠቢባን ይሆኑ ዘንድ ለሚወዱ ሰዎችም ሁሉ ነው እንጂ፥
የደከምኩ ለእኔ ብቻ እንዳይደለ እነሆ አስተውሉ።
27የሕዝቡ መኳንንት ስሙኝ፥
የማኅበሩም አለቆች አድምጡኝ።
28ልጅህንና ሚስትህን፥ ወንድምህንና ወዳጅህን አንተ በሕይወት ሳለህ፥ በገንዘብህ ላይ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በአንተ ላይ” ይላል። አታሠልጥናቸው
ኋላ እንዳትጸጸት፥ ትለምናቸውም ዘንድ እንዳትመለስ፥
በቤትህ ባዕድ ሰው አትሹም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ገንዘብህን ለባዕድ አትስጥ” ይላል።
29አንተ በሕይወት ሳለህ፥
ትንፋሽህም ሳለች ግብርህን አትለውጥ።
30አንተ የልጆችህን እጅ ደጅ ከምትጠና፤
ልጆችህ አንተን ቢለምኑህ ይሻልሃል።
31በምትሠራው ሥራ ሁሉ ብልህ ሁን፤
በተሾምህበትም ሁሉ ራስህን አታስነቅፍ።
32የሕይወት ዘመንህ ሁሉ በአለቀ ጊዜ፤
ፍጻሜህም በደረሰ ጊዜ፥ ያን ጊዜ ገንዘብህን አውርስ።
33አህያህን ገለባ አብላው፤ ጫነው፤ በአለንጋም ግረፈው፤
አገልጋይህንም ቅጣው፤ መግበው፤ ግዛውም።
34አገልጋዮችህንም እንዲሠሩ አድርጋቸው፤ ዕረፍትንም ታገኛለህ፤
ብታቦዝናቸው ግን ይከራከሩህ ዘንድ፥ ከአንተም ነጻ ይወጡ ዘንድ ይወድዳሉ።
35ቀንበር መጫን አንገትን ዝቅ ያደርገዋል፤
አለንጋና እግር ብረትም ለክፉ አገልጋይ ነው።
36አገልጋይህን እንዲሠራ አድርገው፥
አቦዝነህ አታኑረው።
37ቦዘኔነት ብዙ ክፋትን ታስተምራለችና።
38የሚችለውን ያህል ሥራውን ስጠው፤
ባይታዘዝ ግን እግር ብረቱን አጽናበት፤
ነገር ግን ሥጋዊውን ሁሉ አትመነው።
ያለ ምክርም የምትሠራው ሥራ አይኑር፤
39አገልጋይ ቢኖርህ እንደ ራስህ ይሁን፤
በዋጋ ገዝተኸዋልና፥
ደግ አገልጋይም ቢኖርህ እንደ ወንድምህ አድርገው፤ እንደ ራስህም ውደደው።
40ክፉ ነገር ብታደርግበት ግን ይኰበልልብሃል፤ ያመልጥሃልም፤
ከዚህ በኋላ በየት ጎዳና ታገኘዋለህ?#ምዕ. 30 ከቍ. 25 እስከ 40 ያለው በግሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 33 ከቍ. 16 እስከ 33 ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 30: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 30
30
ስለ ልጆች
1ልጁን የሚወድ ሰው በፍጻሜው በእርሱ ደስ ይለው ዘንድ፥
ልጁን መቅጣትን ቸል አይልም።
2ልጁን የሚቀጣ ሰው በእርሱ ደስ ይለዋል፤
በወዳጆቹም ዘንድ ይመካበታል።
3ልጁን ያስተማረ ሰው ጠላቱን ያስቀናል፥
በወዳጆቹም ዘንድ በእርሱ ደስ ይለዋል።
4ከእርሱ በኋላ እንደ እርሱ ያለ ልጅ ተክትዋልና
አባቱ ቢሞትም እንዳልሞተ ይሆናል።
5በሕይወቱም ሳለ በልጁ ደስ ይለዋል፤
ቢሞትም ልቡ አያዝንም።
6ከእርሱ በኋላ ጠላቶቹን የሚበቀል፥
ለወዳጆቹም ዋጋን የሚከፍል ልጅ ተክትዋልና።
7ልጆቹን የሚያባልግ ሰውነቱ ይቈስላል፤
በጩኸታቸውም ጊዜ ልቡ በሕመም ይሠቃያል።
8ያልተገራ ፈረስ ገርጋሪ ይሆናል፤
ያልተቀጣ ልጅም አውታታ ይሆናል፤
9ልጅህን ካቀማጠልኸው ይበረታታብህ ዘንድ ይመለሳል፤
ከእርሱም ጋር ብትጫወት ያሳዝንህ ዘንድ ይመለሳል።
10እንዳያሳዝንህም አትሳቅለት፤
በፍጻሜም ጥርስህን ያረግፍሃል።
11በወጣትነቱ ጊዜ ልጅህን ስድ አትልቀቀው።
በስሕተቱም ጊዜ ቸል አትበለው፤
12በአደገ ጊዜ እንዳያምፅብህ
በልጅነቱ ጊዜ ጎኑን ግረፈው።
13በእርሱ ጥፋት እንዳታፍር
ልጅህን ቅጣው፤ ያገለግልሃልም።
ስለ ጤንነት
14ሰውነቱ ከታመመና ሆዱ ከታሰረ ባለጸጋ፥
ሰውነቱ ጤነኛ የሆነና ሆዱ የተከፈተ ድሃ ይሻላል።
15ሰውነትህ ጤነኛ ይሁን፤
ሆድህም የተከፈተ ይሁን፤
ይህም ከባለጸግነት ሁሉ ይሻላል።
ከባለጸግነትና ከገንዘብም ሁሉ የሰውነት ጤንነት ይሻላል።
16በጤና ከመኖር ባለጸግነት አይመረጥም፤
ከልብ ደስታም የሚሻል ደስታ የለም።
17ከመረረ ኑሮና ከቍርጥማት በሽታ ሞት ይሻላል።
18በተዘጋ አፍ የሚቀርብ መብል
ወደ መቃብር እንደሚወሰድ እህል ነው።
19ለጣዖታት መሠዋት ምን ይጠቅማል?
እነርሱ አይበሉምና፥ እነርሱም አይጠጡምና፥
እነርሱም አያሸትቱምና፥
እግዚአብሔር የቀሠፈውም ሰው እንደዚሁ ነው።
20ጃንደረባ ቆንጆዪቱን ባቀፋት ጊዜ እንደሚያዝን፥
በዐይኖቹ እያየ ያዝናል።
21ነፍስህን አታሳዝን፤
ልብህንም አታስጨንቅ።
22የልቡና ደስታ ለሰው ሕይወቱ ነው፤
የሰውነት ደስታም ዘመንን ያረዝማል።
23ኀዘንን ከአንተ ታርቃት ዘንድ ልብህን አጽናናት፤
ሰውነትህንም አረጋጋት፤
ኀዘን ብዙ ሰዎችን አጥፍታቸዋለችና፤ ኀዘንም የምትጠቅመው የለምና።
24ቅናትና ቍጣ የሕይወት ዘመንን ያሳንሳሉ፤
ኀዘንም ጊዜው ሳይደርስ ያስረጃል።
25አጫጅን እየተከተለ እንደሚቃርም ሰው፤
በእግዚአብሔር በረከት ደረስሁ።
እንደ ወይን ለቃሚም መጭመቂያዬን ሞላሁ።
26ጠቢባን ይሆኑ ዘንድ ለሚወዱ ሰዎችም ሁሉ ነው እንጂ፥
የደከምኩ ለእኔ ብቻ እንዳይደለ እነሆ አስተውሉ።
27የሕዝቡ መኳንንት ስሙኝ፥
የማኅበሩም አለቆች አድምጡኝ።
28ልጅህንና ሚስትህን፥ ወንድምህንና ወዳጅህን አንተ በሕይወት ሳለህ፥ በገንዘብህ ላይ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በአንተ ላይ” ይላል። አታሠልጥናቸው
ኋላ እንዳትጸጸት፥ ትለምናቸውም ዘንድ እንዳትመለስ፥
በቤትህ ባዕድ ሰው አትሹም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ገንዘብህን ለባዕድ አትስጥ” ይላል።
29አንተ በሕይወት ሳለህ፥
ትንፋሽህም ሳለች ግብርህን አትለውጥ።
30አንተ የልጆችህን እጅ ደጅ ከምትጠና፤
ልጆችህ አንተን ቢለምኑህ ይሻልሃል።
31በምትሠራው ሥራ ሁሉ ብልህ ሁን፤
በተሾምህበትም ሁሉ ራስህን አታስነቅፍ።
32የሕይወት ዘመንህ ሁሉ በአለቀ ጊዜ፤
ፍጻሜህም በደረሰ ጊዜ፥ ያን ጊዜ ገንዘብህን አውርስ።
33አህያህን ገለባ አብላው፤ ጫነው፤ በአለንጋም ግረፈው፤
አገልጋይህንም ቅጣው፤ መግበው፤ ግዛውም።
34አገልጋዮችህንም እንዲሠሩ አድርጋቸው፤ ዕረፍትንም ታገኛለህ፤
ብታቦዝናቸው ግን ይከራከሩህ ዘንድ፥ ከአንተም ነጻ ይወጡ ዘንድ ይወድዳሉ።
35ቀንበር መጫን አንገትን ዝቅ ያደርገዋል፤
አለንጋና እግር ብረትም ለክፉ አገልጋይ ነው።
36አገልጋይህን እንዲሠራ አድርገው፥
አቦዝነህ አታኑረው።
37ቦዘኔነት ብዙ ክፋትን ታስተምራለችና።
38የሚችለውን ያህል ሥራውን ስጠው፤
ባይታዘዝ ግን እግር ብረቱን አጽናበት፤
ነገር ግን ሥጋዊውን ሁሉ አትመነው።
ያለ ምክርም የምትሠራው ሥራ አይኑር፤
39አገልጋይ ቢኖርህ እንደ ራስህ ይሁን፤
በዋጋ ገዝተኸዋልና፥
ደግ አገልጋይም ቢኖርህ እንደ ወንድምህ አድርገው፤ እንደ ራስህም ውደደው።
40ክፉ ነገር ብታደርግበት ግን ይኰበልልብሃል፤ ያመልጥሃልም፤
ከዚህ በኋላ በየት ጎዳና ታገኘዋለህ?#ምዕ. 30 ከቍ. 25 እስከ 40 ያለው በግሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 33 ከቍ. 16 እስከ 33 ነው።