መጽ​ሐፈ ሲራክ 32

32
1ሕጉን የሚ​ጠ​ብቅ ሰው መባ ያገ​ባል።
2ትእ​ዛ​ዙን የሚ​ሰማ ሰውም ለድ​ኅ​ነቱ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ይሠ​ዋል።
3ስንዴ የሚ​ያ​ገባ ሰው ዋጋ​ውን ይመ​ል​ሳል።
4ምጽ​ዋ​ትን የሚ​መ​ጸ​ውት ሰውም የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ።
5የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃዱ ክፉ እን​ዳ​ት​ሠራ ነው፤
ፈቃ​ዱም ከበ​ደል ትርቅ ዘንድ ነው።
6ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባዶ​ህን አት​ግባ።
7ይህን ሁሉ ስለ ትእ​ዛዙ አድ​ርግ።
8የጻ​ድቅ ሰው መሥ​ዋ​ዕት ምሠ​ዊ​ያ​ውን ያለ​መ​ል​መ​ዋል፤
መዓ​ዛ​ውም ወደ ልዑል ፊት ይደ​ር​ሳል።
9የጻ​ድቅ ሰው መሥ​ዋ​ዕት ቅዱስ ነው፤
ስም አጠ​ራ​ሩም ሁሉ አይ​ዘ​ነ​ጋ​በ​ትም።
10በደ​ስታ ዐይን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ነው፤
ከመ​ጀ​መ​ሪያ አዝ​መ​ራ​ህም ዐሥ​ራት ማግ​ባ​ትን አት​ተው።
11የሰ​ጠ​ህን ሁሉ ፊት​ህን ደስ እያ​ለው ስጠው፤
ደስ እያ​ለ​ህም የአ​ዝ​መ​ራ​ህን ዐሥ​ራት አግባ።
12እንደ ክብሩ ብዛት መጠን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ​እ​ህን አግባ፤
በእ​ጅህ ከአ​ገ​ኘ​ኸ​ውም በመ​ል​ካም ዐይን አግ​ባ​ለት።
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዋጋ​ህን ይመ​ል​ስ​ል​ሃ​ልና፤
ሰባት እጥፍ አድ​ር​ጎም ይሰ​ጥ​ሃ​ልና፤
14አይ​ቀ​በ​ል​ል​ህ​ምና መማ​ለ​ጃን አታ​ግ​ባ​ለት።
15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ው​ነት ዳኛ ነውና፥
ፊትን አይ​ቶም አያ​ዳ​ላ​ምና የዐ​መፃ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ቀ​በል አይ​ም​ሰ​ልህ።
16ድሃ​ውን ስለ ችግሩ አይ​ለ​የ​ውም፤
የተ​በ​ደለ ሰው​ንም ጩኸት ይሰ​ማል።
17የሙት ልጅ ልመ​ናን ቸል አይ​ልም፤
ባል​ቴት ሴት​ንም የሚ​ያ​ስ​ለ​ቅ​ሳት ሰው ቢኖር፥
18እን​ባ​ንም በፊ​ትዋ ላይ ብታ​ወ​ርድ፥
19እን​ደ​ዚሁ ባስ​ለ​ቀ​ሳት ሰው ላይ እንባ ይወ​ር​ዳል።
20በእ​ው​ነት የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ውን ሰው ይቀ​በ​ለ​ዋል፤
ጸሎ​ቱም እስከ ደመና ትደ​ር​ሳ​ለች።
21የት​ሑት ጸሎት ከደ​መና ታል​ፋ​ለች፥
ወደ እርሱ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ አት​መ​ለ​ስም፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ከ​ሚ​ያ​ያት ድረስ አት​መ​ለ​ስም።
22ለጻ​ድ​ቃን ይፈ​ር​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ቀ​ል​ላ​ቸ​ዋ​ልም፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ርሱ አይ​ዘ​ገ​ይም፤
ክፉ​ዎ​ችን ወገ​ባ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ቀ​ጠ​ቅጥ ድረስ ስለ እነ​ርሱ ፈጽሞ አይ​ታ​ገ​ሥም።
23አሕ​ዛ​ብን ይበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋል፤ ዐመ​ፀ​ኞ​ች​ንም ሁሉ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤
የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም በትር ይሰ​ብ​ራል።
24ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ይከ​ፍ​ለ​ዋል።
25ስለ ሰዎ​ችም ሁሉ እንደ ሥራ​ቸ​ውና
እንደ አካ​ሄ​ዳ​ቸው ፍዳ​ውን ይከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋል።
የወ​ገ​ኖ​ቹን በቀል ይመ​ል​ሳ​ልና፥ በቸ​ር​ነ​ቱም ደስ ያሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ልና።
26በመ​ከራ ጊዜ የሚ​ገኝ ምሕ​ረት
በቃ​ጠሎ ጊዜ ዝናም እንደ ያዘ ደመና ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ