መጽ​ሐፈ ሲራክ 27

27
1በግ​ብ​ዝ​ነት ኀጢ​አ​ትን የሚ​ሠ​ሩ​አት ብዙ​ዎች ናቸው፤
ገን​ዘቡ ይበ​ዛ​ለት ዘንድ የሚ​ወ​ድድ ሰው ግን ዐይ​ኑን ይመ​ል​ሳል።
2ችን​ካር በድ​ን​ጋይ ግንብ መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ተ​ከል፥
በመ​ሸ​ጥና በመ​ግ​ዛት መካ​ከል ኀጢ​አት ትመ​ጣ​ለች።
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት ፈጥኖ ካል​ተ​ጠ​በቀ፥
የቤቱ ውድ​ቀት አይ​ዘ​ገ​ይም።
የሕ​ይ​ወት መመ​ዘኛ
4በወ​ን​ጠ​ፍት ዐሠር ይከ​ማ​ቻል፤
እን​ዲ​ሁም ሁሉ ሰውን ኀጢ​አቱ ታገ​ኘ​ዋ​ለች።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እን​ዲሁ በኀ​ጢ​አ​ተኛ ሰው ንግ​ግር ኀጢ​አት ትከ​ማ​ቻ​ለች” ይላል።
5የሸ​ክላ ዕቃን እሳት ይፈ​ት​ነ​ዋል፤
ሰው​ንም የል​ቡ​ናው ዐሳብ ይፈ​ት​ነ​ዋል።
6ተክል የሚ​ጠ​ብቅ ሰው ፍሬ​ውን ያያል፤
እን​ዲ​ሁም የሰው ነገሩ የል​ቡ​ና​ውን ፈቃድ ይገ​ል​ጥ​በ​ታል።
7ሰውን ሳት​ረ​ዳው አታ​ድ​ን​ቀው፤
ሰውን ከሥ​ራው የተ​ነሣ ይፈ​ት​ኑ​ታ​ልና።
8ጽድ​ቅን ብት​ከ​ተ​ላት ታገ​ኛ​ታ​ለህ፥
እንደ ከበረ ግም​ጃም ትለ​ብ​ሳ​ታ​ለህ።
9ወፍ ከዘ​መዱ ጋር ይኖ​ራል፤
ጽድ​ቅም በሚ​ሠ​ሯት ሰዎች ዘንድ ትኖ​ራ​ለች።
10አን​በሳ የሚ​በ​ላ​ውን ያድ​ናል፤
እን​ዲ​ሁም ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ሯ​ትን ሰዎች ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለች።
11ጻድቅ ሰው ሁል​ጊዜ ጥበ​ብን ያስ​ተ​ም​ራል፤
የሰ​ነፍ ሰው ግን ዕው​ቀቱ እያ​ደረ እንደ ጨረቃ ይጐ​ድ​ላል።
12በሰ​ነ​ፎች ዘንድ ጊዜ​ውን ተጠ​በቅ፤
በብ​ል​ሆች ሰዎች ዘንድ ግን ሁል​ጊዜ ተረዳ።
13የሰ​ነ​ፎች ነገር ያበ​ሳ​ጫል፤
ሣቃ​ቸ​ውም የኀ​ጢ​አት ደስታ ነው።
14ብዙ መሐ​ላን የሚ​ምል ሰው ነገር ፀጕ​ርን ያቆ​ማል፤
የት​ዕ​ቢ​ተኛ ሰው ክር​ክ​ርም ዦሮ ያደ​ነ​ቍ​ራል።
15የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ጠብ ደም ያፋ​ስ​ሳል፤
ክር​ክ​ራ​ቸ​ውም ለሚ​ሰ​ማ​ቸው ሰው ድካም ነው።
የባ​ል​ን​ጀ​ራን ምሥ​ጢር ማው​ጣት እን​ደ​ማ​ይ​ገባ
16የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን ምሥ​ጢር የሚ​ያ​ወጣ ሰው መታ​መ​ኑን ያጠ​ፋል፤
ከዚ​ህም በኋላ እንደ ልቡ የሚ​ሆን ወዳ​ጅን አያ​ገ​ኝም።
17ወዳ​ጅ​ህን ጠብቅ፤ ከእ​ር​ሱም ጋራ ተማ​መን፤
ምሥ​ጢ​ሩን ብታ​ወ​ጣ​በት ግን በኋ​ላው አት​ከ​ተ​ለ​ውም።
18ሰው ጠላ​ቱን እን​ደ​ሚ​ያ​ጠፋ፥
አን​ተም የወ​ዳ​ጅ​ህን ወን​ድ​ም​ነት ታጠ​ፋ​ለህ።
19ወፍ ከእ​ጅህ እን​ደ​ም​ታ​መ​ልጥ፥
እን​ዲሁ ወዳ​ጅህ ከአ​ንተ ያመ​ል​ጣል።
20ምዳቋ ከወ​ጥ​መድ እን​ደ​ም​ታ​መ​ልጥ፥
ከአ​ንተ አም​ልጦ ርቋ​ልና ከዚህ በኋላ አት​ከ​ተ​ለ​ውም።
21ቍስል ቢሆን ባዳ​ኑት ነበር፤ የተ​ሰ​ደ​በ​ንም ሰው ባስ​ካ​ሱት ነበር፤
የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን ምሥ​ጢር የሚ​ያ​ወ​ጣ​ውን ሰው ግን ተስፋ ይቈ​ር​ጡ​በ​ታል።#ግሪኩ “ተስፋ ቢስ ይሆ​ናል” ይላል።
ስለ ግብ​ዝ​ነት
22ክፋ​ቱን ማስ​ተው የሚ​ችል የለ​ምና፤
በዐ​ይኑ የሚ​ጠ​ቅስ ሰው ልቡ​ናው ያማረ አይ​ሆ​ንም።
23ለዐ​ይ​ንህ ግን ከን​ፈ​ሩን ይመ​ጥ​ጥ​ል​ሃል፤
በተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውም ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ን​ሃል፤
ኋላ ግን በቃሉ ይወ​ነ​ጅ​ል​ሃል፤
በተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል​ህም ያጠ​ም​ድ​ሃል።
24የጠ​ላ​ኋ​ቸው ብዙ​ዎች ናቸው፤
ነገር ግን እንደ እርሱ አይ​ደ​ሉም፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ሱን ይጠ​ላል።
25ድን​ጋ​ይን ወደ ላይ የሚ​ወ​ረ​ውር ሰው በራሱ ላይ ትወ​ር​ዳ​ለች፤
የበ​ደል ግር​ፋ​ትም ቍስሉ ይታ​ወ​ቃል።
26ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ጕድ​ጓድ የቈ​ፈረ ሰው፥ እርሱ በው​ስጡ ይወ​ድ​ቃል፤
ወጥ​መ​ድም ያዘ​ጋጀ ሰው ራሱ ይያ​ዝ​በ​ታል።
27ሰው ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ በእ​ርሱ ላይ ትመ​ለ​ሳ​ለች፤
ከየ​ትም እን​ደ​ም​ት​መጣ አያ​ው​ቅም።
28የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ስድ​ባ​ቸ​ውና ሣቃ​ቸው
እንደ አን​በሳ ያድ​ኑ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ቀ​ሉ​አ​ቸ​ዋ​ልም።
29በጻ​ድቅ ሰው መው​ደቅ ደስ የሚ​ላ​ቸው ሰዎች በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛሉ፤
የሚ​ሞ​ቱ​በ​ትም ጊዜ ሳይ​ደ​ርስ መቅ​ሠ​ፍት ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።
30ቍጣና መዓ​ትም የሚ​ያ​ስ​ጸ​ይፉ ናቸው፤
በኀ​ጢ​አ​ተኛ ሰውም ዘንድ ጸን​ተው ይኖ​ራሉ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ